Tag: statutory interpretation

ማጣቀሻዎች እና ህግ አተረጓጎም

ማጣቀሻዎች እና ህግ አተረጓጎም

በህግ የተደነገጉ ወይም በልማድ የዳበሩ የህግ አተረጓጎም ስልቶችን በመጠቀም አግባብነት ያለውን የህግ ትርጉም ማበጀት አስቸጋሪ በሚሆንባቸው ሁኔታዎች ከተጻፈው ህግ ወጣ ብሎ አግባብነት ያላቸውን ምንጮች መዳሰስ ጥሩ አማራጭ ተደርጎ ይወሰዳል፡፡ በተለያዩ አገራት የሚገኙ ፍርድ ቤቶች ውጫዊ ማጣቀሻዎችን /Extrinsic Aids/ የመጠቀም ፍላጎታቸውና ልማዳቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ መጨመር አሳይቷል፡፡[1] በስፋት ተቀባይነት ካገኙ ማጣቀሻዎች መካከል ሐተታ ዘምክንያት፣ /Legislative History/ የህጉ ታሪካዊ ዑደት /Legislative Evolution/ ዓለም ዓቀፍ ስምምነቶች፣ /International Agreements/ የሌሎች አገራት ህግ እና የፍርድ ቤት ውሳኔዎች እንዲሁም የምሁራን ስራዎች ሰፊ ተቀባይነት አግኝተዋል፡፡[2]

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት በበርካታ መዝገቦች በማጣቀሻ የታገዙ ውሳኔዎች ሰጥቷል፡፡ በእርግጥ ጥቅም ላይ የዋሉበት መንገድ ሲታይ ግልጋሎታቸው እንደ ደጋፊ ማለትም እንደ ማጠናከሪያ ምክንያት ነው፡፡ የሚጠቀሱት ምንጮች አከራካሪ የህግ ጭብጦችን ለመፍታት ቀጥተኛ አስተዋጽኦ አላደረጉም፡፡ ሁሉንም ውሳኔዎች ማካተት ባይቻልም በተወሰኑት ላይ የተደረገው ከፊል ዳሰሳ እንደሚከተለው ይቀርባል፡፡ Continue reading “ማጣቀሻዎች እና ህግ አተረጓጎም”