Tag: human trafficking

በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር /ረቂቅ/ የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር…/2011

በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር የወጣ አዋጅ

በሰው የመነገድ፣ ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር እና በህገ-ወጥ መንገድ ለስራ ወደ ውጭ አገር መላክ ወንጀሎች በዜጎች አካል፣ ህይወት እና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ እና ለሰብአዊ መብት ጥሰት እያገለጡ የሚገኙ ወንጀሎች መሆናቸውን በመገንዘብ ፤

በሰው የመነገድ እና ሰውን በህገ ወጥ መንገድ ድንበር ማሻገር ወንጀልን ለመከላከል እና ለመቆጣጠር የወጣው አዋጅ ቁጥር 909/2007 ግልጽነት የሚጎድለው፣ ከሌሎች ህጎች ጋር የማይጣጣምና ለችግሩ በቂ ምላሽ የማይሰጥ ሆኖ በመገኘቱ በአዲስና በተሟላ የሕግ ማዕቀፍ መተካት በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ድሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት አንቀጽ 18 መሰረት በማንኛውም መንገድ በሰው መነገድ በመከልከሉ እንዲሁም በሰው የመነገድ በተለይም በሴቶችና ሕጻናት መነገድን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠርና ወንጀል ፈጻሚዎችን ለመቅጣት እና ሰውን  በሕገ-ወጥ መንገድ በየብስ፣ በባህርና በአየር ማስወጣትና ማስገባት ለመከላከል የሚያስችሉ ፕሮቶኮሎችን የተባበሩት መንግስታት ድርጅት በማውጣቱና ኢትዮጵያም ስምምነቱን ያጸደቀች በመሆኑ የማስፈጸሚያ ዝርዝር ህግ ማውጣት አስፈላጊ በመሆኑ፤

መንግስት ሰዎች በተፈጥሮ እና በህግ የተጎናጸፉትን መብትና ጥቅም የማክበር እና የማስከበር ኃላፊነት ያለበት በመሆኑ በወንጀል መከላከል፣ ወንጀል ፈጻሚዎችን በህግ ተጠያቂ ማድረግ፣ የተጎጂዎች ጥበቃና መልሶ ማቋቋም በተለይም ለወንጀሎቹ ተጋላጭ የሆኑ የህብረተሰቡ ክፍሎችን ተደራሽ የሚያደርግና የተጎጂዎችን ዕድሜ፣ ጾታና ልዩ ፍላጎት ያማከል ተግባር መፈጸም እና ዓለም አቀፍ ትብብርን ለማጠናከር የሚያስችል የህግ ማዕቀፍ ማውጣት እና ስርዓት መፍጠር አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀጽ 55 (5) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ Continue reading “በሰው የመነገድ እና ሰውን በሕገ-ወጥ መንገድ ድንበር የማሻገር ወንጀልን ለመከላከልና ለመቆጣጠር /ረቂቅ/ የወጣ አዋጅ”