Tag: ethiopian law of agency

ስለ ውክልና- የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም

ውክልና

ተወካይ የሆነ ሰው ወካዩ ለሆነው ሌላ ሰው እንደራሴ ሆኖ አንድ ወይም ብዙ ህጋዊ ስራዎች በወካዩ ስም ለማከናወን የሚገባበት ውል

አንድ ተወካይ የውክልና ስራ በሚፈጽምበት ጊዜ የወካዩን ህጋዊ ሁኔታዎችን የመለወጥ ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ ይህም በመሆኑ ተወካዩ ለወካዩ ፍጹም ታማኝ የመሆን እና የወካዩን ጥቅም ሙሉ ለሙሉ የማስጠበቅ ግዴታ ተጥሎበታል፡፡ ስለሆነም ተወካዩ ስራውን በሚያከናውንበት ጊዜ ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባው የወካዩን ጥቅም ብቻ በመሆኑ የጥቅም ግጭት ባለበት ሁኔታ ተወካዩ በስራው አፈጻጸም ጥንቃቄ ሊያደርግ ይገባል፡፡ ምክንያቱም የጥቅም ግጭት በሚፈጠርበት ጊዜ አንድ ተወካይ ከራሱ ጥቅም ይልቅ የወካዩን ጥቅም ሊያስቀድም ይችላል ተብሎ አይታሰብም፡፡ ስለዚህም ተወካዩ የራሱን ጥቅም የሚመለከት ጉዳይ ሲያጋጥመው ሁኔታውን ለወካዩ ሳያሳውቅና ወካዩ ሳይስማማ ስራውን እንዳይፈጽም ይከለከላል፡፡ Continue reading “ስለ ውክልና- የሰበር ችሎት የህግ ትርጉም”