Tag: Ethiopian labour law

‘አሠሪና ሠራተኛ ሕግ’ አዲስ መጽሐፍ

‘አሠሪና ሠራተኛ ሕግ’ በገበያ ላይ ውሏል፡፡ በዩኒቨርሳል የመጽሐፍት መደብር (አራት ኪሎ)ያገኙታል፡፡

ማውጫ        DOWNLOAD

የሰበር ውሳኔዎች ማውጫ    DOWNLOAD

የሕግጋት ማውጫ        DOWNLOAD

ዋቢ መጻህፍትና ጽሑፎች   DOWNLOAD

የቃላት ማውጫ             DOWNLOAD

የተመረጡ ገጾች                              

ዝውውር እና የአሠሪው ስልጣን፡ የሰበር አቋም ሲፈተሽ     DOWNLOAD

የኃይማኖት ተቋም ሠራተኞች                         DOWNLOAD

በጥፋት ምክንያት ሠራተኛን ስለማሰናበት         DOWNLOAD

የሥራ መደብ መሰረዝ                          DOWNLOAD

ህገ መንግስታዊ መብት ይቃጠላል?—የዓመት ፈቃድ መተላለፍ ውጤት

አንቀጽ 77 ንዑስ አንቀጽ 5 በአማርኛውና በእንግሊዝኛው እንደሚከተለው ይነበባል፡፡

“በዚህ አዋጅ መሰረት የሥራ ውሉ የተቋረጠ ሠራተኛው ያልወሰደው የዓመት ፈቃድ ታስቦ በገንዘብ ይከፈለዋል”

A worker whose contract of employment is terminated under this proclamation is entitled to his pay for the leave he has not taken

ድንጋጌውን በአማርኛ ሆነ በእንግሊዘኛ ለሚያነብ ሰው ይዘቱ እንከን የማይወጣለትና ትርጉም የማይሻ ስለመሆኑ መረዳት አይሳነውም፡፡ ሠራተኛው ያልወሰደው የዓመት ዕረፍት ፈቃድ ሲባል ያልተጠቀመበት፣ ዕረፍት ያልወጣበት፣ ሳይሰጠው የቀረ ፈቃድ ማለት ነው፡፡ ግልጽ ህግ ትርጉም እንደማያስፈልገው ግልጽ ነው፡፡ ስለሆነም “ለሠራተኛው የሚከፈለው ያልወሰደው ሳይሆን ከሁለት ዓመት በላይ ያልተላለፈው የዓመት ፈቃድ ነው” ወደ ሚል አቅጣጫውን የሳተ መደምደሚያ የሚያደርሰን ምክንያት የለም፡፡ ሊኖርም አይችልም፡፡ የዓመት ፈቃድ ከተላለፈ ወይም ካልተወሰደ “ሠራተኛው ውሉ ሲቋረጥ ሊያገኝ በሚገባው የክፍያ መብት ላይ ገደብ ይጥላል” የምንል ከሆነ ይህንኑ አቋማችንን ከዓመት ፈቃድ አስፈላጊነት፣ ከአሠሪና ሠራተኛ ህጉ መሰረታዊ ዓላማና ተዛማጅ ህገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎች ጋር ልናስታርቀው ይገባል፡፡ ከሁለት ዓመት በላይ የተላለፈ የዓመት ፈቃድ “ይቃጠላል” የሚል አመለካከት የሕጉን መሠረታዊ ዓላማዎች የሚሸረሽር እንደመሆኑ ከህግና ከስነ-አመክንዮ ሊታረቅ የሚችልበት መንገድ የለም፡፡

የዓመት ፈቃድ የማግኘት መብት በሥራ ውል ሆነ በህብረት ስምምነት ወይም በሥራ ደንብ እና በመሳሰሉት ሊጠብ ሆነ ሊገደብ የማይችል በህግ የተደነገገ፤ በህገ መንግስቱ የታወቀ አነስተኛ የስራ ሁኔታ ነው፡፡ የዓመት ፈቃድን ጨምሮ ሌሎች አነስተኛ የስራ ሁኔታዎችን በህግ መደንገግ ያስፈለገበት ዋና ምክንያት አነስተኛ የመደራደር አቅም ያለውን ሠራተኛ ከአሠሪ ኢ-ፍትሐዊ ተጽዕኖ ለመከላከል ሲባል ነው፡፡ አነስተኛ የስራ ሁኔታዎች ባልተከበሩበት ሁኔታ የኢንዱስትሪ ሰላም ሊሰፍን አይችልም፡፡ Continue reading “ህገ መንግስታዊ መብት ይቃጠላል?—የዓመት ፈቃድ መተላለፍ ውጤት”

አሠሪና ሠራተኛ ህግ፡ የሰበር ችሎት እንደተረጎመው

Update: መስከረም 4 ቀን 2012

መልካም ዜና! የታተመውን አሰሪና ሰራተኛ ህግ ጨምሮ ሶስት መጽሐፍትን ከ Google Play Store

ላይ በነጻ በማውረድ በሞባይላችሁ ላይ ጭናችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። ለማውረድ ከዚህ በታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ፡

 

 

 

አሰሪና ሰራተኛ ህግ

 

 

 

 

 

የአስተዳደር ህግ መግቢያ

 

 

 

በላልበልሃ፡ የጠበቃ ቀልዶችና የችሎት ገጠመኞች

 

 

 

 

The Revised Family Code of Ethiopia

 

 

 

 

Criminal Procedure code of Ethiopia

 

 

 

 

 

በ2008 ዓ.ም. ለፍሬ ለማብቃት ካቀድኳቸው ሥራዎች ውስጥ ሁለቱ ተጠናቀው አንደኛው ደግሞ ተገባዶ በማየቴ በተለምዶ ‘እጥፍ ድርብ’ የሚባለው ዓይነት ባይሆንም ትልቅ ደስታና እፎይታ ተሰምቶኛል፡፡ ይንንም ለ Ethiopian Legal Brief ጎብኚዎች በተለይም ደግሞ ለድረ ገጹ ቋሚ ተከታታዮች (followers and subscribers) ለማጋራት በማሰብ ብሎም ቅድመ ህትመት ለአንባቢ መተዋወቂያ ይሆን ዘንድ የአንደኛውን ሥራ የይዘት ማውጫ፤ የውሳኔዎች ማውጫ፤ የህግጋት ማውጫ፤ ዋቢ መጻህፍትና የቃላት ማውጫ ከቅንጭብ ጽሑፎች (የተመረጡ ገጾች) ጋር በዚህ ገጽ ላይ ለማቅረብ እወዳለው፡፡

በመጀመሪያ የሶስቱም ያልታተሙ ሥራዎች ርዕስና ገጽ ብዛት እነሆ!

  1. አሠሪና ሠራተኛ ህግ፡ የሰበር ችሎት እንደተረጎመው (ቅጽ 1 ገጽ ብዛት 411)
  2. የአስተዳደር ህግ መግቢያ (ገጽ ብዛት 265)
  3. Judicial and Statutory Definitions of Words and Phrases (365 pages)

አሠሪና ሠራተኛ ህግ፡ የሰበር ችሎት እንደተረጎመው

በዚህ ሥራ ከ1998 እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው የታተሙ (ቅጽ 1 እስከ 18) እንዲሁም ያልታተሙ በጠቅላላይ ከ240 በላይ በሚሆኑ የሰበር ውሳኔዎች ላይ ዳሰሳ ተደርጓል፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት የካቲት 2007 ዓ.ም. ላይ ሥራው ሲጀመር ከይዘት አንጻር ዋነኛ ትኩረት የተደረገው ገላጭ የሆነ ዘዬ በመከተል የሰበር ችሎት ትርጉም የሰጠባቸውን ጉዳዮች በየፈርጁና በየርዕሱ በመለየት የህጉን ይዘት በጥልቀት መፈተሸ ነበር፡፡ ሆኖም ‘የሌሎች አገራት ልምድ’ እንዲካተት ተደጋጋሚ አስተያየት በመቅረቡ ባደጉትና ባላደጉት አገራት የአሠሪና ሠራተኛ ህግ ይዘቱና አፈጻጸሙ በከፊል ተቃኝቷል፡፡

በመጽሐፉ ውስጥ የተጠቀሱ ህግጋትና የሰበር ውሳኔዎች በቀላሉ ማግኘት እንዲቻል የውሳኔዎች ማውጫ (Table of Cases) እና የህግጋት ማውጫ (Table of Legislations) ለብቻው ተዘጋጅቷል፡፡ የቃላት ማውጫው (Index) የቃላት ሳይሆን የተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች መጠቆሚያ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል፡፡

ማውጫዎቹንና የተመረጡ ጽሑፎችን ለማውረድና ለማንበብ DOWNLOAD የሚለውን link ተጫኑት፡፡

ማውጫ                             DOWNLOAD

የሰበር ውሳኔዎች ማውጫ              DOWNLOAD

የሕግጋት ማውጫ                    DOWNLOAD

ዋቢ መጻህፍትና ጽሑፎች             DOWNLOAD

የቃላት ማውጫ                      DOWNLOAD

የተመረጡ ገጾች                              

ዝውውር እና የአሠሪው ስልጣን፡ የሰበር አቋም ሲፈተሽ     DOWNLOAD

የኃይማኖት ተቋም ሠራተኞች                         DOWNLOAD

በጥፋት ምክንያት ሠራተኛን ስለማሰናበት         DOWNLOAD

የሥራ መደብ መሰረዝ                          DOWNLOAD