Tag: Ethiopian federalism

የመንግስታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣ አዋጅ (ረቂቅ)

ተዛማጅ ሰነዶች

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስታት ግንኙነቶች የፖሊሲ ማዕቀፍ

DOWNLOAD

የመንግስታት ግንኙነት ረቂቅ አዋጅ ላይ የተዘጋጀ አጭር ማብራሪያ

DOWNLOAD

አዋጅ ቁጥር——–20…. ዓ.ም

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣ አዋጅ (ረቂቅ)

የመንግስታት ግንኙነት ስርዓትን ለመወሰን የወጣ አዋጅ

ሀገራችን ኢትዮጵያ ፌደራላዊና ዴሞክራሲያዊ የመንግስት አደረጃጀት ስርአትን የምትከተል እንደመሆኗ መጠን ዘላቂ ሰላምን ለማስፈን፣ ዋስትና ያለው ዴሞክራሲን ለማረጋገጥ፣ ፈጣን ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልማትን ለማስቀጠልና አንድ የፖለቲካና የኢኮኖሚ ማህበረሰብን ለመገንባት ይቻል ዘንድ ከተናጠል ጥረቶች ይልቅ የየእርከኑን አካላት አቅሞች በተገቢው መንገድ አቀናጅቶና አዋህዶ ዘርፈ-ብዙ የልማትም ሆነ የመልካም አስተዳደር ተግባራትን ለማከናወን የሚያስችሉ መደበኛ የመንግስታት ግንኙነቶችን በግልፅ መደንገግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በስራ ላይ ባለው ፌደራላዊ የመንግስት አደረጃጀት ውስጥ የፌደራልም ሆነ የክልል መንግስታት የተናጠልና የወል ስልጣንና ሀላፊነቶች በህገ-መንግስቱ ተለይተው የተቀመጡ ቢሆንም የየእርከኑ መንግስታት በወል ከተሰጣቸው ሀላፊነት ባሻገር በተናጠል በየተመደቡላቸው ስልጣንና ተግባራት ተቀራርቦና እርስ በርስ ተናቦ መስራትና ተገቢ ሆኖ ሲገኝ የጋራ ፖሊሲዎችንና ስትራቴጂዎችን ነድፎ በዉጤታማነት ለመንቀሳቀስ የሚያግዝ ትብብራዊ የግንኙነት ማዕቀፍ እንደ ሚያስፈልጋቸው በመታመኑ፤

በፌደራላዊ ስርዓተ-መንግስት ውስጥ በመንግስታት መካከል የሚካሄዱ የእርስ በርስ ምክክሮችና፣ የሚደረጉ የትብብር ስምምነቶች ከስርዓቱ ባህርይ የሚመነጩ እንደ መሆናቸው መጠን ለስርዓቱ ዘለቄታ ተፈላጊ የሆኑ የጋራ አስተሳሰቦችን በመያዝና በማጠናከር ስርዓቱ በየጊዜው እየጎለበተ የሚሄድበትን አሰራር መዘርጋት በማስፈለጉ፤

በፌደራልና በክልል መንግስታት፣ እንዲሁም በራሳቸው በክልሎች መካከል እርስ በርስ ሲካሄዱ በቆዩ ግንኙነቶች እስከ አሁን የታዩትን ጥንካሬዎች ለማስቀጠልና ያጋጠሙ ወይም ወደፊት ሊያጋጥሙ የሚችሉ ክፍተቶችን ለመሙላት፣ ፌደራላዊ ስርዓቱንም ሆነ የሀገሪቱን ዲሞክራሲያዊ አንድነት ለማጠናከር ብሎም በየእርከኑ መንግስታትና አቻ ተቋማቱ መካከል በመርህ ላይ የተመሰረተ ጠንካራ የትብብር ስርዓት መፍጠር ለፌደራላዊ ስርዓቱ ጤናማነትና ቀጣይነት ጉልህ ድርሻ ያለው በመሆኑ፤

እያንዳንዱ መንግስት የተሰጠውን ስልጣንና ሃላፊነት ለመወጣት የራሱን ዕቅድ በሚነድፍበትና በሚፈጽምበት ጊዜ በተናጠል ከመስራቱ የተነሳ የወጪ መደራረብና የጊዜ ብክነት እንዳይደርስና ከተገልጋዮች ፍላጎት መለዋወጥና ማደግ ጋር በተያያዘም የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርዶችን በጋራ በመንደፍና አዳዲስ አሰራሮችን በመዘርጋት እንዲሁም በክልሎች መካከል የልምድ ልውውጦችን በማካሄድ በመካከላቸው የሚታየውን ወጣ-ገባነትና የጥራት ልዩነቶችን ማጥበብና ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖር ማድረግ ተገቢ ሆኖ በመገኘቱ፤

ለዚሁ ያመች ዘንድም የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት የሚመራበት ራሱን የቻለ ህግ ማውጣትና ገቢራዊ ማድረግ በማስፈለጉ ይህ አዋጅ ታውጇል፡፡

ክፍል አንድ

ጠቅላላ ድንጋጌዎች

 1. አጭርርዕስ

ይህ አዋጅ “በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግሥታት ግንኙነት ስርዓት መወሰኛ አዋጅ ቁጥር………/20…. ዓ.ም” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

 1. ትርጓሜ

የቃሉ አገባብ ሌላ ትርጉም የሚያሰጠው ካልሆነ በስተቀር በዚህ አዋጅ ውስጥ፡-

1/ “ክልል” ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ-መንግስት አንቀፅ 47 ስር የተጠቀሱት ሲሆን ለዚህ አዋጅ ዓላማ ሲባል በሕግ የተሰጣቸው ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ አስተዳደሮችን ይጨምራል፡፡

2/ “መንግስት ወይም መንግስታት” ማለት እንደ አግባብነቱ የፌደራልና ወይም የክልል መንግስታትን ይገልጻል፡፡

3/ “የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት” ማለት ይህንን አዋጅ በመከተል እንዳስፈላጊነቱ የፌደራልና የክልል መንግስታት በመካከላቸው፣ እንዲሁም የክልል መንግሥታት በጋራ ወይም በጣምራ በተሰጣቸው ስልጣንና በሚያገናኙዋቸው ጉዳዮች ላይ የሚመሰርቱት የቀጥታ ወይም የጎንዮሽ ግንኙነት ሲሆን ግንኙነቶቹ የሚመሩበትን መርሆዎች፣ አሰራሮችና አደረጃጀቶችን የሚያካትት ነው፡፡

4/ “የግንኙነት መድረክ” ማለት እንዳግባብነቱ ሀገር-አቀፉ የህግ አዉጪ አካላት ግንኙነት መድረክ፣ አገር-አቀፉ የህግ አስፈፃሚዎች ግንኙነት መድረክ፣ አገር-አቀፉ የዳኝነት አካላት ግንኙነት መድረክ፣ ሀገር-አቀፉ የአስፈፃሚዎች ዘርፋዊ ግንኙነት መድረኮች፣ የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች ግንኙነት መድረክ ወይም የክልል መንግስታት ግንኙነት መድረክ ነው፡፡

5/ “ሀገር-አቀፍ የአስፈፃሚዎች ዘርፋዊ የግንኙነት መድረኮች” የሚለው ሀረግ የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ ማናቸውም የፌዴራልና አቻ ክልላዊ የዘርፍ አስፈፃሚ መስሪያ ቤቶች፣ የህግ አስከባሪና በፌዴራልና በክልል መንግስታት አወቃቀር ውስጥ ተመሳሳይ ተግባራትን የሚያከናዉኑ ሌሎች የዘርፍ መስሪያ ቤቶች በጋራና በሚያገናኟቸው ጉዳዮች ላይ ለመምከር በዚህ አዋጅ መሰረት የተቋቋመን መድረክ የሚያጠቃልል ነው፡፡

6/ “የማዕቀፍ ስልጣን” ማለት በአንዳንድ የስልጣን ዘርፎች ለፌደራልና ለክልል መንግሥታት ተመሳሳይ ስልጣንና ሀላፊነት የተሰጠበት የስልጣን ክፍፍል ስርዓት ሆኖ ክልሎች በዘርፉ የሚያወጧቸው መንግስታዊ ፖሊሲዎችና ሕጎች ከፌደራሉ መንግስት ፖሊሲዎችና ሕጎች ጋር የተጣጣሙ እንዲሆኑ በማዕቀፍነት የሚያገለግል ስልጣን ነው፡፡

7/ “ሴክሬታሪያት” ማለት በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የመንግሥታት ግንኙነትን የሚመለከቱ ተግባራትን ለማስተባበርና ለማሳለጥ አስተዳደራዊና ቴክኒካዊ ጉዳዮችን እንዲያከናውን ሃላፊነት የተሰጠው አካል ነው፡፡

8/ ማንኛውም በወንድ ፆታ የተገለፀው የሴትንም ፆታ ይጨምራል፡፡

 1. የተፈጻሚነት ወሰን

1/   ይህ አዋጅ በፌደራልና በክልል መንግሥታት፣ እንዲሁም በራሳቸው በክልል መንግሥታት መካከል በጋራ እና በጣምራ በተሰጣቸው ስልጣኖች ዙሪያ በሚካሄዱ ግንኙነቶች ላይ ተፈጻሚ ይሆናል፡፡

2/   በዚህ አንቀጽ ንኡስ አንቀጽ (1) ስር የሰፈረው አጠቃላይ ድንጋጌ እንደተጠበቀ ሆኖ አዋጁ በተለይ ተፈጻሚ የሚሆንባቸው ቁልፍ የመንግስታት ግንኙነቶችና ተቋማት ከዚህ በታች የተመለከቱት ይሆናሉ፡-

ሀ/ በሀገር-አቀፉ የህግ አውጪዎች ግንኙነት መድረክ አማካኝነት በፌደራልና በክልል መንግስታት መካከል የሚካሄድ ቀጥታ ግንኙነት፤

ለ/ በሀገር-አቀፉ የህግ አስፈጻሚዎች ግንኙነት መድረክ አማካኝነት በፌደራልና በክልል መንግሥታት መካከል የሚካሄድ ቀጥታ ግንኙነት፤

ሐ/ በሀገር-አቀፉ የሕግ ተርጓሚዎችግንኙነት መድረክ አማካኝነት በፌደራልና በክልል የዳኝነት አካላት መካከል የሚካሄድ ቀጥታ ግንኙነት፤

መ/ የፌደራልና የክልል ዋና ኦዲተር መስሪያ ቤቶችን ጨምሮ በሀገር-አቀፉ የዘርፍ አስፈፃሚ መድረኮች አማካኝነት በፌደራሉ መንግስት አስፈጻሚ አካላትና በክልል አቻዎቻቸው መካከል በተናጠል የሚካሄድ ዘርፍ-ተኮር ግንኙነት፤

ሠ/ እንደ አጀንዳዎቹ ስፋትና ጥልቀት ሁለት ወይም ከዚያ በላይ በሆኑ ወይም በሁሉም የክልል መንግሥታት የተናጠል ወይም የጋራ መድረኮች አማካኝነት የሚካሄድ ሁሉንአቀፍ ወይም ዘርፍ-ተኮር የጎንዮሽ ግንኙነት፤

ረ/ በፌደሬሽን ምክር ቤትና በክልሎች መድረክ አማካኝነት የሚካሄድ የፌደራልና የክልል መንግስታት ግንኙነት፤

ሰ/ እንደ አስፈላጊነቱ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚካሄዱ ሌሎች ግንኙነቶች፣ የሚደራጁ የጋራ መድረኮችና በተናጠልም ሆነ በጋራ የሚዋቀሩ የዚሁ ግንኙነት አሳላጭ ተጨማሪ አደረጃጀቶች፡፡

ክፍል ሁለት

መሰረታዊ መርሆዎች

 1. መሰረታዊ መርሆዎች

በዚህ አዋጅ መሰረት የፌደራልና የክልል መንግስታት እንዲሁም የክልሎች የርስበርስ ግንኙነቶች የሚከተሉትን መርሆዎች በጥብቅ በማክበርና በመከተል ይካሄዳሉ፡፡

1/ የሕገ-መንግሥትን የበላይነት ማክበር፤

2/ እኩልነትና የርስበርስ መከባበር፤

3/ ምክክርና ድርድር፤

4/ ሀገራዊ ራዕዮችንና ዕሴቶችን ማጎልበት፣

5/ ግልፅነትና ተጠያቂነት፤

6/ አሳታፊነትና ውጤታማነት፤

7/ ትብብርና የጋራ መግባባት፤

ክፍል ሶስት

ስለመንግስታት ግንኙነቶች ስርአት አመሰራረት፣ ተቋማዊ አደረጃጀትና ተግባር

 1. 5. ስለምስረታ

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ መደበኛ የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት ከዚህ በኋላ “የመንግስታት ግንኙነት ስርዓት” ተብሎ የሚጠራው በዚህ አዋጅ ተመስርቷል፡፡

 1. 6. የመንግስታት ግንኙነት አደረጃጀት

የመንግስታት ግንኙነት መድረኮች የሚከተሉት  ናቸው፡-

1/ ሀገር-አቀፉ የሕግ አውጭዎች ግንኙነት መድረክ፣

2/ ሀገር–አቀፉ የሕግ አስፈጻሚዎች ግንኙነት መድረክ፣

3/ ሀገር-አቀፉ የህግ ተርጓሚዎች ግንኙነት መድረክ፣

4/ ሀገር-አቀፉ የአስፈፃሚዎች ዘርፋዊ ግንኙነት መድረክ፣

5/ የፌደሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች ግንኙነት መድረክና

6/ የክልል መንግሥታት የግንኙነት መድረኮች፡፡

ንኡስ ክፍል አንድ

ስለ ሀገር-አቀፉ የሕግ አውጪዎች የግንኙነት መድረክ

 1. የመድረኩ አባላት ተዋጽኦ

1/ ሀገር-አቀፉ የህግ አዉጪዎች የግንኙነት መድረክ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

ሀ/ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣

ለ/ የፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣

ሐ/ የየክልሉ፣የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ አስተዳደር ምክር ቤቶች አፈ-ጉባኤዎች፣

መ/ የደቡብ ክልል ብሄሮች፣ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፤

2/ መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የፌደራልም ሆነ የክልል ምክር ቤቶች ቋሚ ኮሚቴዎች ሰብሳቢዎችና ሌሎች አካላት እንደ ተገቢነታቸው በአባልነት ወይም በአስረጂነት እንዲሳተፉ ሊጋብዝ ይችላል፡፡

 1. 8. የመድረኩ ተግባርና ኃላፊነት

ሀገር-አቀፉ የህግ አዉጪዎች ግንኙነት መድረክ በዚህ አዋጅ መሰረትየሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶችይኖሩታል፡-

1/ በሕገ-መንግስቱ ለፌደራልና ክልል መንግስታት በጋራ የተሰጡ ስልጣንና ኃላፊነቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ የሚያስችሉ፣ እርስበርስ የተጣጣሙና የተመጋገቡ ሕጎች እንዲያወጡ ምክክር ያደርጋል፣ አፈፃፀማቸውን ይከታተላል፣ ይገመግማል፤

2/ በሕገ-መንግስቱ በተናጠል ህግ የማውጣት ስልጣን እንደተጠበቀ ሆኖ በየደረጃው የሚገኙ ምክርቤቶችይህንን ተግባራዊ ከማድረጋቸው በፊት ሌላኛውን የስልጣን እርከን በአሉታዊ መንገድ የማይጎዳ ስለመሆኑ ይመክራል፣ መግባባት እንዲፈጠር ይጥራል፣ ይኸው በተግባር ላይ መዋሉን ይከታተላል፤

3/ ሃገራዊ እንድምታ ባላቸው ጉዳዮች ላይ በመምከር የህዝቡን የጋራ ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ የሚያስችሉ ሕጎች እንዲወጡ ይመክራል፣ አብሮነትን ያጠናክራል፣ የሃገር ግንባታን ለማሳካት የተደነገጉ ሕጎችን አፈፃፀም በቅርብ ይከታተላል፣ እንዲሁም በፌደራልና በክልል መንግሥታት የወጡ ወይም ወደፊት የሚወጡ ህጎችን ተቃርኖ በማስተካከል አንደኛው ከሌላው ጋር እንዲጣጣሙ የሚያደርጉ ተግባራትን ያከናውናል፤

4/ በፌደራሉ መንግስት ፖሊሲዎች፣ ሕጎችና ስትራቴጂዎች ላይ ተቀራራቢ የአፈፃፀም ደረጃ እንዲኖር የጋራ መግባባት ይፈጥራል፤

5/ በአስፈፃሚ አካላት መካከል የተደረሱ ስምምነቶች ሕገ-መንግስታዊ ድንጋጌዎችን የተከተሉ ስለመሆናቸው በጋራ ይመክራሉ፣ በአስፈፃሚዎች የጋራ ስምምነቶች ተግባራዊነትና አፈፃፀም ላይ ክትትል ያደርጋል፣ የእርምት እርምጃዎች እንዲወሰዱ ይመክራሉ፤

6/ የሕዝብ ተወካዮችና የክልል ምክር ቤቶች አባላት የህዝብ ውክልና ግዴታቸውን ለመወጣት ወደመረጣቸው ህዝብ ወርደው ተግባርና ሀላፊነቶቻቸውን በጋራና በተቀናጀ መንገድ እንዲፈፅሙ ያስተባብራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡

ንኡስ ክፍል ሁለት

ስለ ሀገር-አቀፉ የሕግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ

 

 1. 9. የመድረኩ አባላት ተዋጽኦ

1/ ሀገር-አቀፉ የህግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

ሀ/ የኢ.ፌ.ዴ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር፣

ለ/ የሁሉም ክልሎች ርእሳነ-መስተዳድሮች፣

ሐ/ የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣

2/ መድረኩ አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነባቸው ሌሎች የፌደራል ወይም የክልል ተቋማት ኃላፊዎች እንደ ተገቢነታቸው በአባልነት ወይም በአስረጂነት እንዲሳተፉ ሊጋብዝ ይችላል፡፡

 1. 10. የመድረኩ ተግባርና ኃላፊነት

ሀገር-አቀፉ የህግ አስፈፃሚ አካላት ግንኙነት መድረክ  በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-

1/ የፌደራሉ መንግስትና የክልል አስፈፃሚ አካላት ግንኙነቶች የበላይ አካል ሆኖ፣ ሁለቱንም የመንግስት እርከኖች በሚመለከቱ ጉዳዮች ላይ ውይይትና ምክክሮችን ያደርጋል፣ በሀገር-አቀፍ የፖሊሲ ሀሳቦችና አጠቃላይ በሆኑ ጉዳዮች ላይ ዉይይትና ምክክሮችን ያካሂዳል፤

2/ በሀገር-አቀፍ ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎች፣ ፕሮግራሞችና ዕቅዶች ላይ ውይይቶችን ያካሂዳል፣ ይመካከራል፣ ወሳኝ በሆኑ ጉዳዮች ላይ የጋራ መግባባት እንዲፈጠር ያደርጋል፣ የተደረሰባቸውን የመግባቢያ ስምምነቶች አፈፃፀም በተቀናጀ መንገድ ይከታተላል፣ ይገመግማል፣ ይመራል፤

3/ ሀገራዊ አንድምታ ባላቸው የዘላቂ ሰላም፣ የዲሞክራሲ፣ የመልካም አስተዳደር፣ እንዲሁም ፈጣንና ፍትሃዊ የማህበረ-ኢኮኖሚያዊ ልማት ጉዳዮች ላይ ይመክራል፣በሚያጋጥሙ ችግሮች ዙሪያ የመፍትሄ ሃሳቦችን ያመነጫል፤

4/ በሕገ-መንግስቱ ለፌደራል መንግስቱና ለክልሎች በጋራ የተሰጡ ስልጣንና ኃላፊነቶችን ተፈፃሚ ለማድረግ የጋራ አፈፃፀም ስልት ይነድፋል፣ ይገመግማል፣ ይመራል፤

5/ የፌደራል መንግስት ስልጣንና ሃላፊነቱን በክልሎች ተግባራዊ ሲያደርግ ከክልሎች ጋር ይመክራል፣ አስተያየቶቻቸውን ያዳምጣል፤

6/ በዘርፋዊ የአስፈፃሚ መድረኮች ደረጃ ዕልባት ያላገኙና ዘርፍ ተሻጋሪ የሆኑ ጉዳዮች ሲያጋጥሙ በነዚሁ ላይ ይመክራል፣ ክትትልና ድጋፍ ያደርጋል፤

7/ ሃገር-አቀፍ አገልግሎት በሚሰጡ ተቋማት የሥራ አፈጻጸም ዙሪያ ምክክር ያደርጋል፣ እንዲሁም ክልሎች በውክልና በሚያከናዉኗቸው የፌደራሉ መንግሥት ስራዎች ላይ የወጪ አሸፋፈንን በተመለከተ ውይይትና ምክክር ያካሂዳል፣ መመሪያዎችን ይሠጣል፤

8/ በመንግስታት ግንኙነት የፖሊሲ አፈጻጸምና ስትራቴጅያዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያል፣ ምክክሮችን ያካሂዳል፣ መግባባት ላይ ይደርሳል፣ አስፈላጊ ውሳኔዎችን ያሳልፋል፡፡

9/ ስርዓተ-ፆታ በሁሉም የመንግስታት ግንኙነቶች ተገቢውን ትኩረት ማግኘቱን ይከታተላል፡፡

ንኡስ ክፍል ሶስት

ስለሀገር-አቀፉ የህግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ

 

 1. 11. የመድረኩ አባላት ተዋጽኦ

1/ሀገር-አቀፉ የህግ ተርጓሚዎች የግንኙነት መድረክ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

ሀ/ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዚደንት፣

ለ/ የክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤቶች ፕሬዚደንቶች፣

2/ መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የፌደራልም ሆነ የክልል የዳኝነት አካላት ወይም ሌሎች ተቋማት ባልደረቦች እንደ ተገቢነቱ በአባልነት ወይም በአስረጂነት እንዲሳተፉ ሊጋብዝ ይችላል፡፡

 1. 12. የመድረኩ ተግባርና ሀላፊነት

በሕገ-መንግስቱ አንቀፅ 80 ስር የተደነገገውን የፍርድ ቤቶች ጣምራነትና የዉክልና ጉዳይ አስመልክቶ ቀደም ሲል ተቋቁመው በመስራት ላይ ያሉት ፍትህና ዳኝነት-ነክ የምክክር አካላት ባሉበት ሁኔታ ተጠናክረው የሚቀጥሉ ሲሆን በዚህ አዋጅ የተደራጀው መድረክ የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-

1/ የዳኝነት አካሉ በቴክኖሎጂ የታገዘ፣ ተደራሽ፣ ቀልጣፋና የተገልጋዩን ህብረተ-ሰብ እርካታ በየጊዜው እየፈተሸና እያሳደገ በሚኬድባቸው አግባቦች ላይ ይመክራል፣ የጋራ ስልቶችን ይነድፋል፤

2/ የሕግ የበላይነትና ፍትሃዊነት በሚረጋገጥባቸው ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ያካሂዳል፣ አፈጻጸማቸውን በቅርብ ይከታተላል፤

3/ የፌደራል ሕጎች በክልል ደረጃ የተቀራረበ አተረጓጎም እንዲኖራቸው ምክክር ያደርጋል፣ የመፍትሄ እርምጃዎችን ይወስዳል፤

4/ ነፃና ገለልተኛ የሆነና የሕዝብ አመኔታን ያተረፈ የዳኝነት ሥርዓት እንዲገነባ ይጥራል፤

5/ በውክልና በሚሰጥ የፌደራል የዳኝነት ስልጣንና ተያያዥነት ባላቸው ሌሎች አስተዳደራዊ ጉዳዮች ላይ ውይይቶችን ያካሂዳል፣ የአፈጻጸም ስልት ይቀይሳል፤

6/ ከዳኝነት ስርዓቱ ጋር በተገናኙ ጉዳዮች ላይ የአቅም ግንባታና ሌሎች የለዉጥ ፕሮግራሞች ተቀናጅተው እንዲፈፀሙ ያደርጋል፣ መመሪያዎችን ይሰጣል፤

7/ የፍትህና የዳኝነት ስርአቱን ይበልጥ በሚያጎለብቱ ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፣ ይወያያል፡፡

ንኡስ ክፍል አራት

ስለ ሀገር-አቀፉ የአስፈፃሚዎች ዘርፋዊ የግንኙነት መድረክ

 

 1. የመድረኩ አባላት ተዋጽኦ

1/ ሀገር-አቀፉ የህግ አስፈፃሚዎች ዘርፋዊ የግንኙነት መድረክ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

ሀ/ የየዘርፉ የፌደራል መንግስት መስሪያ ቤቶች የበላይ ሀላፊዎች፤

ለ/ የዘጠኙ ክልሎች፣ እንዲሁም የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ አስተዳደሮች የየዘርፉ መስሪያ ቤቶች ኃላፊዎች፡፡

2/ መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የሌሎች አካላት ወይም ተቋማት ተወካዮች በስብሰባው ላይ በአባልነት ወይም በአስረጂነት እንዲሳተፉ ሊጋብዝ ይችላል፡፡

 1. የመድረኩ ተግባርና ኃላፊነት

መድረኩ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-

1/ በየዘርፉሀገር-አቀፍ ጥቅሞችን በሚመለከቱ ዋና ዋና ጉዳዮች ላይ በጋራ ይመክራል፣

2/ የክልሎችን ስልጣን፣ ጥቅሞችና ፍላጎቶች በሚመለከቱ የፌዴራል መንግስት ዘርፍ ተኮር ፖሊሲዎች፣ ስትራቴጂዎችና ዕቅዶች ዝግጅትና አፈፃፀም ላይ ይመክራል፣ ክልሎች የሚሰጧቸውን ሃሳቦችና አስተያየቶች ያዳምጣል፣

3/ በጋራና በማዕቀፍ ስልጣኖች አተገባበር ዙሪያ የሚዘጋጁ የረዥም፣ የመካከለኛና የአጭር ጊዜ ዕቅዶችና ፕሮግራሞች የሚቀናጁበትንና የሚተሳሰሩበትን ስርዓት ይፈጥራል፣ በጋራ እንዲፈጸም ያደርጋል፣

4/ በየዘርፎቹ የአገልግሎት አሰጣጥ ጥራትና የአፈፃፀም ደረጃ ዙሪያ ውይይቶችን ያካሂዳል፣ የጋራ ስልቶችን ይነድፋል፣

5/ በክልል ደረጃ በሚተገበሩ ዘርፍ-ተኮር ሀገራዊ ዕቅዶችና ፕሮግራሞች ዝግጅት፣ አፈጻፀም፣ ክትትልና ግምገማ ላይ ይመክራል፣

6/ የምርጥ ተሞክሮዎች ልዉዉጥ የሚካሄድበትና ወደ ተቀራራቢ የአፈጻጸም ደረጃ የሚደረስበትን መንገድ በጋራ ይቀይሳል፣ ይመክራል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፤

7/ በየክልሉ የሚመዘገቡትን የስራ አፈጻጸም ዉጤቶች ወደ ተመሳሳይ ደረጃ ለማድረስ የሚያስችል የአቻ ግምገማ ሥርዓት በጋራ ይቀይሳል፣ ተግባራዊ በሚሆንበት አግባብ ላይ ምክክር ያደርጋል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፤

8/ የአስፈጻሚዉን ዘርፋዊ ተግባራት በሚያጠናክሩ ሌሎች ተዛማጅ ጉዳዮች ላይ እንዳስፈላጊነቱ ይወያያል፣ መመሪያዎችን ይሰጣል፡፡

 1. 15. የጋራ ጉባኤ ስለማቋቋም

ሁለትና ከዚያ በላይ የሆኑ ዘርፋዊ የአስፈፃሚ አካላት የግንኙነት መድረኮች አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኙት በጋራ የሚታቀፉበት አቢይ መድረክ ወይም ጉባኤ የማቋቋም መብት አላቸው፤ ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቱንም የዚህን አዋጅ ድንጋጌዎች መንፈስ ተከትለው ሊወስኑ ይችላሉ፡፡

ንኡስ ክፍል አምስት

ስለፌደሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች ግንኙነት መድረክ

 

 1. 16. የመድረኩ አባላት ተዋጽኦ
 2. የፌደሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች ግንኙነት መድረክ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

ሀ/ የፌዴሬሽን ምክር ቤት አፈ-ጉባኤ፣

ለ/ የየክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዬዎች፣

ሐ/ የየክልሉ ርዕሳነ-መስተዳድሮች፣

መ/ የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ አስተዳደሮች ከንቲባዎች፣

ሠ/ የገንዘብ ሚኒስቴር

ረ/ የሰላም ሚኒስትር፤

ሰ/ የገቢዎች ሚኒስቴር

 1. 2. መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የሌሎች አካላት ወይም ተቋማት ተወካዮች በስብሰባው ላይ በአባልነት ወይም በአስረጂነት እንዲሳተፉ ሊጋብዝ ይችላል፡፡
 2. የመድረኩ ተግባርና ኃላፊነት

የፌዴሬሽን ምክር ቤትና የክልሎች ግንኙነት መድረክ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-

1/ የፌደራሉ መንግሥት ለክልሎች በሚሰጠው ድጎማ ቋትና ክፍፍል እንዲሁም በሕገ-መንግስቱ ለፌደራልመንግሥቱና ለክልል መንግሥታት በተሰጡ የጋራ ገቢዎች ክፍፍል ላይይወያያል፣በመካከላቸው የርስበርስ መግባባት የሚፈጠርበትን ሁኔታ ያመቻቻል፣

2/ የብሄሮች፣ ብሄረ-ሰቦችና የህዝቦችን አብሮነትና የጋራ ተጠቃሚነት ለማጎልበት በሚያስችሉ መሰረታዊ ጉዳዮች ላይይመክራል፣ እንዲሁምበመካከላቸው በሚታዩ የግንኙነት አዝማሚያዎች ላይ አስቀድሞ በመወያየት በየደረጃው ለሚገኙ አስፈፃሚ አካላት የሚጠቅሙ ምክረ-ሃሳቦችን ይሰጣል፣

3/ በብሄር-ብሄረ-ሰቦችና ህዝቦች፣ በተለይም አናሳ ቁጥር ባላቸው ማህበረ-ሰቦች አያያዝ ላይ ውይይቶችን ያካሂዳል፣ ምርጥ ልምዶችን ያስፋፋል፣ በአያያዝ ላይ የሚስተዋሉ ችግሮች ቢኖሩ በአፋጣኝ የሚፈቱባቸውን ስልቶች ይቀይሳል፣ አፈጻጸማቸውንም በቅርብ ይከታተላል፣ ይደግፋል፣

4/ በክልሎችና በተለያዩ ማህበረሰቦች መካከል ለግጭት መንስኤ በሚሆኑ ጉዳዮችና አፈታታቸው ላይ ምክክር ያደርጋል፣የተከሰቱና የተፈቱ ግጭቶችና አለመግባባቶች ቀጣይነት ያለው ቅራኔ በማይፈጥርና ወንድማማቻዊ ትስስሮችን ይበልጥ በሚያጎለብት መንገድ ለማስተካከል የሚያስችል ስልት ይነድፋል፣ አፈጻጸሙን ይከታተላል፡፡

ንኡስ ክፍል ስድስት

ስለክልል መንግሥታት የግንኙነት መድረክ

 

 1. 18. የመድረኩ አባላት ተዋጽኦ
 2. 1. የክልል መንግሥታት የጋራ ግንኙነት መድረክ የሚከተሉት አባላት ይኖሩታል፡-

ሀ/ የየክልሉ ምክር ቤት አፈ-ጉባዬዎች፣

ለ/ የሁሉም ክልሎች ርዕሳነ-መስተዳድሮች፣

ለ/ የአዲስ አበባ ከተማና የድሬዳዋ አስተዳደሮች አፈ-ጉባዔዎች እና ከንቲባዎች፡፡

 1. 2. መድረኩ አስፈላጊ ናቸው ብሎ ያመነባቸው የሌሎች አካላት ወይም ተቋማት ባልደረቦች በስብሰባው ላይ በአባልነት ወይም በአስረጂነት እንዲሳተፉ ሊጋብዝ ይችላል፡፡
 2. 19. የመድረኩ ተግባርና ሃላፊነት

የክልል መንግሥታት የጋራ ግንኙነት መድረክ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሩታል፡-

1/ የሀገር-አቀፍ ፖሊሲዎች፣ ስትራተጂዎችና ዕቅዶች አፈፃፀም በክልሎች ላይ ያሳደራቸውን ወይም የሚያሳድራቸውን በጎና አሉታዊ ተፅእኖዎች ይገመግማል፣ እንዳስፈላጊነቱ የማሻሻያ ሃሳቦችን ለፌደራል መንግሥቱ ያቀርባል፣

2/ በአንድ ክልል ውሳኔ ያገኘ ጉዳይ በሌሎች ክልሎች ተፈፃሚነት እንዲኖረው የጋራ መግባባት የሚደረስበትን አሰራር ይዘረጋል፣ አተገባበሩን ይከታተላል፣

3/ በልማት፣ በመልካም አስተዳደርና በመሰረታዊ ሰብዓዊ መብቶችና ነጻነቶች አያያዝና አጠባበቅ ረገድ ተቀራራቢ አፈፃፀም እንዲኖር የጋራ ስልት ይቀይሳል፣ የተሞክሮ ልውውጥ እንዲደረግ ሁኔታዎችን ያመቻቻል፣

4/ የፌደራል መንግሥቱን ልዩ ትኩረት በሚሹ ጉዳዮች ላይ ይመክራል፣ የተደረሰበትን የጋራ አቋም ለሚመለከተው አካል ያሳውቃል፣ አፈጻጸሙንም ይከታተላል፣

5/ ክልሎችን በጋራ የማስተሳሰር ፋይዳ ያላቸውና ድንበር ተሻጋሪ የሆኑ ችግሮችን ለመፍታት የሚያስችሉ ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች እንዲነደፉ ያደርጋል፣ በተነደፉት ፕሮግራሞችና ፕሮጀክቶች ጠቀሜታ ላይ ይወያያል፣ የውሳኔ አስተያየቱን አግባብ ላለው አካል ያስተላልፋል፡፡

 1. 20. የተለያዩ መድረኮችን ስለማቋቋም

ሁለት ወይም ከዚያ በላይ የሆኑ ተጎራባች ክልሎች እንዳስፈላጊነቱ ርእሳነ-መስተዳድሮችን ወይም የዘርፍ አስፈፃሚ አካላት የበላይ ሃላፊዎችን ያቀፉ የጋራ መድረኮችን የማቋቋም መብት አላቸው፤  የነዚህ መድረኮች ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች ይህንን አዋጅ መሰረት አድርጎ በሚወጣ መመሪያ ይወሰናል፡፡

ክፍል አራት

የመንግሥታት ግንኙነት  የስብሰባና የአሰራር ስነ-ስርዓት

 1. 21. የግንኙነት ትስስር

የመንግሥታት ግንኙነት አደረጃጀቶችና ተግባራት ተቀናጅተው የሚመሩት በሚከተለው የአሰራር ስርዓት ይሆናል፡-

1/ ሀገር-አቀፍ የሕግ አስፈፃሚው እና የሕግ ተርጓሚው አካላት የግንኙነት መድረኮች አፈፃፀማቸውን፣ ያጋጠሟቸውን ችግሮችና ሕግ እንዲወጣላቸውየሚፈልጓቸውን ጉዳዮች በሚመለከት ለሕግ አውጪው የግንኙነትመድረክ ያቀርባሉ፡፡

2/ ሀገር-አቀፉ የአስፈፃሚዎች ግንኙነት መድረክም ከሴክሬታሪያቱ በሚቀርብለት ሪፖርት ላይ ከተወያየ በኋላ ውጤቱን ለሀገር-አቀፉ የሕግ አውጭዎች ግንኙነት መድረክ ያስተላልፋል፡፡

3/ ሀገር-አቀፉ የሕግ አውጪዎች ግንኙነት መድረክ በበኩሉ ከሀገር-አቀፉ የአስፈፃሚዎች ግንኙነት መድረክ የተላለፈለት ሪፖርት የዳኝነት ስርአቱን የሚመለከት ሆኖ ያገኘው እንደሆነ ለሀገር-አቀፉ የሕግ ተርጓሚ አካላት ግንኙነት መድረክ እንዲደርስ ያደርጋል፡፡

 1. 22. ስለግልፅነትና የተጠያቂነት አሰራር

በዚህ አዋጅ መሰረት የሚካሄዱ የመንግሥታት ግንኙነቶች ከዚህ በታች የተመለከቱትን ዘዴዎች ተግባራዊ ያደርጋሉ፡-

1/ የመንግስታት ግንኙነት መድረኮች ግንኙነት የተደረገባቸውን ጉዳዮች በሚመለከት በብዙሃን መገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት ለህዝብ ይፋዊ መግለጫዎችን ይሰጣሉ፡፡

2/ የመንግሥታት ግንኙነት መድረኮች የርስበርስ ምክክሮችን ካካሄዱ በኋላ ወሳኝ በሆኑ የጋራ ጉዳዮቻቸው ላይ የሚደርሱባቸውን ስምምነቶች፣ ያሳለፏቸውን ውሳኔዎችና አፈፃፀማቸዉን የሚያሳዩ የመግባቢያ ሰነዶች ይፈራረማሉ፣ ስምምነቶቹንም ለየምክር ቤቶቻቸው ያሳውቃሉ፡፡

3/ የአስፈፃሚዎች ዘርፋዊ የግንኙነት መድረኮች አፈፃፀማቸውን በተመለከተ ለሀገር-አቀፉ የአስፈፃሚዎች ግንኙነት መድረክ ሪፖርት ያቀርባሉ፡፡

4/ የመንግስታት ግንኙነት መድረኮች በየደረጃው የሚያሳልፏቸውን ውሳኔዎች ተፈጻሚ በማያደርጉ አካላት ላይ እንዳግባብነቱ በትይዩ ለሚገኙ የክልል ርዕሳነ-መስተዳድሮችና ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ሪፖርት በማድረግ ተገቢው የእርምት እርምጃ በወቅቱ እንዲወሰድ ያደርጋሉ፤ ጉዳዩንም በብዙሀን መገናኛ ዘዴዎች አማካኝነት ያጋልጣሉ፡፡

 1. 23. ስለመወያያ አጀንዳዎች አቀራረፅና አቀራረብ

1/ በመንግሥታት ግንኙነት መድረኮች ውይይት የሚደረግባቸው ርዕሰ-ጉዳዮች በሚመለከታቸው የመድረኩ አባላት ስምምነት ላይ የተደረሰባቸው ይሆናሉ፡፡

2/ የፌደራልም ሆኑ የክልል አካላት በመወያያ አጀንዳዎች አቀራረፅ ወቅት እኩል የመሳተፍ ዕድል ይኖራቸዋል፡፡

3/ አጀንዳ የመቅረፁን ሂደት የየመድረኮቹ ሴክሬታሪያቶች ያስተባብራሉ፡፡

 1. ስለ ስብሰባ አመራር

1/ የትኛውም የመንግስታት ግንኙነት መድረክ  ስብሰባ በጋራ አመራር ይካሄዳል፡፡

2/ የፌደራል መንግስቱ የስራ ሃላፊዎች ሰብሳቢና የክልል አቻዎቻቸው በዙር በምክትል ሰብሳቢነት ይመራሉ፡፡

 1. ስለ ስብሰባ ጊዜና የውሳኔ አሰጣጥ ስነ-ስርዓት

1/ የመንግሥታት ግንኙነቶች መድረክ መደበኛ ስብሰባውን በስድስት ወር አንድ ጊዜ ያካሂዳል፤ ሆኖም እንዳስፈላጊነቱ አስቸኳይ ስብሰባዎችን ከማካሄድ በዚህ ድንጋጌ አይታገድም፡፡

2/ ከመድረኩ አባላት መካከል 2-3ኛ የሚሆኑት በስብሰባው ላይ ከተገኙ ምልአተ-ጉባኤ ይሆናል፡፡

3/ ለግንኙነት መድረኮች ቀርበው ውይይት የተደረገባቸውና ውሳኔ የሚሹ ጉዳዮች በተቻለ መጠን በስምምነት እና በድርድር እልባት እንዲያገኙ ይደረጋል፡፡

4/ ማናቸውም የውሳኔ ሃሳብ በስምምነትም ሆነ በድርድር የማይቋጭ ሆኖ የተገኘ እንደሆነ በስብሰባው ላይ በተገኙት የመድረኩ አባላት ሶስት-አራተኛ ድምጽ የመጨረሻ ውሳኔ ያገኛል፡፡

ክፍል አምስት

ስለሀገር-አቀፍፉ የመንግስታት ግንኙነት ሴክሬታሪያትና ሌሎች ፅህፈት ቤቶች መቋቋምና ተግባር

 1. 26. ስለ ሴክሬታሪያቱ መቋቋምና ተጠሪነት

1/ በሀገር-አቀፍ ደረጃ የመንግስታት ግንኙነትን የሚያስተባብር ህጋዊ ሰውነት ያለው ከዚህ በኋላ “ሴክሬታሪያቱ” እየተባለ የሚጠራ አካል በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል፡፡

2/ የሴክሬታሪያቱ ተጠሪነት ለሀገር-አቀፉ የሕግ አስፈፃሚዎች የግንኙነት መድረክ (ለጠቅላይ ሚኒስትሩ) ይሆናል፤

3/ የፌደራልና የክልል መንግሥታት በጋራ ተስማምተው ሴክሬታሪያቱን የሚመሩ ተሿሚዎችን ይመድባሉ፡፡

4/ ሴክሬታሪያቱ ለስራው አስፈላጊ ባለሙያዎችና ሌሎች ሰራተኞች ይኖሩታል፡፡

5/ ለሴክሬታሪያቱ ስራ ማስኬጃ የሚያስፈልገዉን በጀት የፌደራልና የክልል መንግሥታት በማዋጣት በጋራ ይመድባሉ፤ ዝርዝሩ ይህንን አዋጅ ለማስፈፀም በሚወጣ ደንብ ይወሰናል፡፡

6/ የበጀት አፈፃፀሙን ኦዲት በተመለከተ ክልሎችና የፌደራሉ መንግሥት በጋራ ተስማምተው በሚሰይሙት አካል እንዲከናወን ሊያደርጉ ይችላሉ፡፡

 1. 27. የሴክሬታሪያቱ ተግባርና ኃላፊነት

ሴክሬታሪያቱ በዚህ አዋጅ መሰረት የሚከተሉት  ተግባርና ሃላፊነቶች  ይኖሩታል፡-

1/ መንግሥታቱ በጋራ የነደፏቸውን ፕሮግራሞች፣ ዕቅዶችና የደረሱባቸዉን ስምምነቶች አፈፃፀም ይከታተላል፤ የመንግሥታት ግንኙነትን የሚመለከቱ ተግባራትን የማስተባበርና የማሳለጥ እንዲሁም ሙያዊና ቴክኒካዊ ስራዎችን ያከናውናል፤

2/ ግንኙነቶቹ ለስርዓቱ መጎልበት፣ ለህብረቱ መጠናከርና ለህዝቦች ወዳጃዊ ትስስር የሚያስገኙትን ፋይዳ ያጠናል፣ መድረኮቹ በሀብት አጠቃቀምና በጥራት ረገድ ውጤታማ እንዲሆኑ ይሰራል፣

3/ የየመድረኮቹን ውጤታማነት በመከታተል፣ በግንኙነቶቹ ዙሪያ የሚታዩትን ክፍተቶች በጥናት ላይ ተመስርቶ ይለያል፣ ግንኙነቶችን የተመለከቱ የዳሰሳ ጥናቶችን በማካሄድ፣ የአፈፃፀም ሪፖርቶችን፣ የመፍትሄ ሃሳቦችን እያዘጋጀ፣ ለሀገር-አቀፉ የአስፈፃሚዎች ግንኙነት መድረክ ያቀርባል፡፡

4/ አለመግባባቶችንና ግጭቶችን ሊፈጥሩ የሚችሉ ጉዳዮችን አስቀድሞ በመለየት የመድረኩ የትኩረት አጀንዳዎች እንዲሆኑ ያደርጋል፤

5/ በመንግሥታቱ መካከል የመረጃ ልውውጡ ሳይቋረጥ እንዲሳለጥ ይሰራል፤

6/ በተመሳሳይ ጉዳዮች የሌሎች ፌደሬሽኖች ልምዶችን በመቀመርና ከሀገሪቱ ነባራዊ ሁኔታዎች ጋር በማጣጣም በጥቅም ላይ እንዲውሉ ሃሳብ ያቀርባል፣ ሲወሰንም ይህንኑ ተከታትሎ ያስፈጽማል፤

7/ በመንግሥታት ግንኙነቶች ዙሪያ የሚታዩ የግንዛቤ ክፍተቶች እንዲቀረፉ ትምህርታዊ ማብራሪያዎችን ይሰጣል፤

8/ በየደረጃው የተቋቋሙ መድረኮችና ሌሎች አደረጃጀቶች እንዲጠናከሩ ሙያዊ ድጋፍ ይሰጣል፤

9/ ግንኙነቶቹን የሚያጠናክሩና በሀገር-አቀፉ የአስፈጻሚዎች ግንኙነት መድረክ የሚሰጡትን ሌሎች ተዛማች ተግባራት ያከናውናል፡፡

 1. 28. ስለ ሌሎች ፅህፈት ቤቶች መቋቋም

በዚህ አዋጅ መሰረት የተቋቋሙትን የቀጥታም ሆነ የጎንዮሽ መንግሥታዊ ግንኙነቶችና በየዘርፉ የተደራጁትን መድረኮች የሚያስተባብሩ የተለያዩ ጽህፈት ቤቶች እንዳስፈላጊነቱ  ሊቋቋሙ ይችላሉ፡፡

 1. 29. የክልሎችና የሌሎች መድረኮች ፅህፈት ቤቶች ተግባርና ኃላፊነት

በዚህ አዋጅ መሰረት የተቋቋሙ የክልልና የዘርፍ መድረኮች ጽህፈት ቤቶች የሚከተሉት ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች ይኖሯቸዋል፡-

1/ የመንግሥታት ግንኙነት ስርዓቱን አጠቃላይ ጤናማነትና ውጤታማነት ይከታተላሉ፤

2/ በመንግሥታቱ ግንኙነቶች ዙሪያ የጥናትና ምርምር ስራዎችን ያካሂዳሉ፣

3/ ግንኙነቶችን የሚመለከቱ የአፈፃፀም ሪፖርቶችን እያዘጋጁ ለጋራ መድረኮች ያቀርባሉ፣

4/ ግንኙነቶችን የሚመለከቱ የድጋፍ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ፣

5/ የግንኙነቶቹን አካሄድና ውጤታማነት በተመለከተ ለመገናኛ ብዙሀንና ለተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ወቅታዊ መረጃዎችንና ማብራሪያዎችን ይሰጣሉ፣

6/ የየመድረኮቹን ስብሰባዎች ያመቻቻሉ፤

7/ የመንግሥታት ግንኙነትን የሚያጠናክሩ ሌሎች ተዛማጅ ተግባራትን ያከናዉናሉ፡፡

 1. ስለ ሌሎች ኮሚቴዎች

1/ የመንግሥታት ግንኙነት መድረኮች ስራዎቻቸዉን ለማሳለጥ የሚያግዙ ልዩ ልዩ ኮሚቴዎችን እንዳስፈላጊነቱ ሊያቋቁሙ ይችላሉ፡፡

2/ የኮሚቴዎቹ ተጠሪነት ለያቋቋሟቸው የግንኙነት መድረኮች ይሆናል፡፡

3/ የነዚህ ኮሚቴዎች ዝርዝር ተግባርና ሀላፊነቶች በያቋቋሟቸው አካላት ይወሰናሉ፡፡

ክፍል ስድስት

ልዩ ልዩ ድንጋጌዎች

 1. 31. ተፈጻሚነት ስለማይኖራቸው ህጎች

ይህንን አዋጅ የሚቃረን ማናቸውም ህግ፣ ደንብ፣ መመሪያ ወይም የተለመደ አሰራር በዚህ አዋጅ ውስጥ በተሸፈኑት ጉዳዮች ላይ ተፈጻሚነት አይኖረውም፡፡

 1. 32. መመሪያ የማውጣት ስልጣን

1/ ሀገር-አቀፉ የህግ አስፈጻሚዎች የግንኙነት መድረክ ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉትን መመሪያ የማውጣት ስልጣን አለው፡፡

2/ ይህንን አዋጅና በአዋጁ መሰረት የሚወጡትን ዝርዝር መመሪያዎችን በአዋጁ የተቋቋሙትና ጉዳዩ የሚመለከታቸው ሌሎች የመንግሥታት ግንኙነት መድረኮች ሊያወጡ ይችላሉ፡፡

 1. 33. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ አዋጅ በፌደራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የፀና ይሆናል፡፡

አዲስ አበባ፣ —— ቀን 20…. ዓ.ም

ሳህለወርቅ ዘውዴ

የኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፓብሊክ ፕሬዚደንት

 

The virtues of true decentralization – Addis Standard

Source: Op:Ed: The virtues of true decentralization – Addis Standard

Belachew Mekuria, PhD, For Addis Standard

Addis Abeba, June 18/2019 – In an earlier piece for AS, I highlighted the need for empowered regional states in our federal arrangement so as to enable us ‘establish and sustain one economic community.’ The praxis of our federalism is hardly in sync with the constitutional promises of a truly self-governing structures in social, economic and political dimensions. The role of regional governments in looking after the socio-economic and political affairs of their people is dashed aside to the margins rendering them dependent on the ‘almighty’ center that, under the guise of building single economic community, controls the formulation and implementation of the country’s policies spanning every aspect of the body politic. I intend to briefly explain why true decentralization is one of the many long overdue reforms that the country ought to address.

Centralized Economy, Decentralized Poverty

It is desirable to pursue economic policies that embrace local conditions and endeavor to meet the needs of the people who are not only poor, but in relative terms, are getting poorer by the day. Creation of single economic community is excessively referenced to legitimize the central control of economic policy making that is supported by a relatively over-capacitated central bureaucracy. House of Federation has the mandate to propose laws that help establish and sustain one economic community for enactment by the House of Peoples’ Representatives. While an attempt is made to institutionalize a centralized economic policy making, implementation and monitoring infrastructure, it has not led to an overall improvement in well-being and livelihoods. As a result, the capacity to design sound policies for accelerated economic growth at regional level is highly undermined; poverty still remains ubiquitous; some experiencing it more than others.

Though there are a number of areas that call for genuine decentralization, I limit the discussions to three key areas for devolution of power to the respective regions having profound implication on empowering members of the federation.

Click HERE to read the remaining story.

የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም በክልሎች ላይ ያለው ስልጣን ህገ-መንግስታዊ ስላለመሆኑ – ክፍል ፩

በህዝብ እንባ ጠባቂ ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር 211/1992 አንቀጽ 4 መሰረት በፌደራሉ መንግስት የተቋቋመው ፌደራል እንባ ጠባቂ በክልል መንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላትና ባለስልጣናት የሚፈፀሙ የአስተዳደር ጥፋቶችን የመመርመር ስልጣን ተሰጥቶታል፡፡ በተመሳሳይ መልኩ የኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁ. 210/1992 አንቀጽ 4 አዋጁ በማንኛውም ክልል ውስጥ በሚፈፀሙ የሰብዓዊ መጣስ ጉዳዮችም ላይ ስልጣን እንደሚኖረው ይደነግጋል፡፡ የሁለቱም አዋጆች አንቀጽ 4 አፈላጊነት ሆነ ህገ-መንግስታዊነቱ በሚገባ የተመከረበትና የታሰበበት ካለመሆኑም በላይ በተግባር የክልሎችን የዲሞክራሲያዊ ተቋም ግንባታ ጅምሮ ከማዳከም በቀር ተጨባጭ ፍሬ አላስገኘም፡፡

የዚህ ጽሁፍ ዋና ዓላማ ተቋሙ ሆኖ ኮሚሽኑ በክልሎች ላይ የተሰጣቸው ስልጣን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ-መንግስት የማይፈቅደው ስለሆነም ህገ-መንግስታዊ መሰረት እንደሌለው ብሎም ከተግባራዊ ምክንያቶች አንጻር የማያስኬድና ለአፈፃፀም የማይመች ስለመሆኑ አሳማኝ መከራከሪያዎች ማቅረብ ነው፡፡

ቀጥሎ በሚቀርው ዳሰሳ ውስጥ በተለየ ሁኔታ ካልተመለከተ በስተቀር እንባ ጠባቂ የሚለው ቃል በተመሳሳይ መልኩ ኮሚሽኑንም ያጠቃልላል፡፡ በሁለቱም ማቋቋሚያ አዋጆች ላይ የሚገኙት ድንጋጌዎች ከይዘት አንጻር ብቻ ሳይሆን ከአንቀጽ አቀማመጥ ጀምሮ ተመሳሳይነት አላቸው፡፡ በተጨማሪም ኮሚሽኑ ሆነ ተቋሙ ስያሜያቸው ቢለያይም በአሰራርም በተግባርም በስልጣንም /Power/ ሁለቱም ያው እንባ ጠባቂዎች ናቸው፡፡ በሁለቱ መካከል ያለው ቀጭን ልዩነት የስልጣን ክልል (jurisdiction) ልዩነት ነው፡፡ የህዝብ እንባ ጠባቂ ተቋም የአስተዳደር ጥፋቶችን ኮሚሽኑ ደግሞ የሰብዓዊ መብት መጣስ ጉዳዮችን በተመለከተ የመመርመር የመከታተል፣ የመቆጣጠርና የመመርመር ስልጣን አላቸው፡፡ በሌላ አነጋገር ኮሚሽኑ የሰብዓዊ መብት ጉዳዮች እንባ ጠባቂ ሲሆን ተቋሙ ደግሞ የአስተዳደር ጥፋቶች እንባ ጠባቂ ተብሎ ሊፈረጅ ይችላል፡፡ በዚህ የተነሳ ከዚህ በታች የሚቀርቡት መከራከሪያዎች ላይ በጥቅሱ እንባ ጠባቂ የሚለው ቃል ለሁለቱም በወካይነት ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ በመከራከሪየነት የሚነሱት መሰረታዊ ነጥቦች የሚከተሉት ናቸው፡፡

 • እንባ ጠባቂ የማቋቋም ህገ-መንግስታዊ ግዴታ
 • ራስን በራስ የማስተዳደር መብት
 • እንባ ጠባቂ-እንደ ፓርላማ ክንፍ
 • የተቋሙ መፍትሔ ይዘትና አፈጻጸም
 • የአቅም ውስንነት
 • ለተቋሙና ተሿሚው ያለው ከበሬታ

እንባ ጠባቂ የማቋቋም ህገመንግስታዊ ግዴታ

እንባ ጠባቂ በክልል መንግስታት ላይ ስልጣን ሊኖረው ይገባል ወይስ አይገባም? የሚለው ጥያቄ ተቋሙን ሆነ ኮሚሽኑን በኢትዮጵያ ውስጥ በዝርዝር ህግ ለማቋቋም ከታሰበበት ጊዜ አንስቶ እስከ አሁን ድረስ ገሃድ የወጣ ክርክርና ውይይት አልጋበዘም፡፡ በክልል መንግስታት ዘንድም ውስጥ ውስጡን የጉርምርምታ ምንጭ ቢሆንም ጉዳዩ በጭብጥነት ተመዞ የመነጋገሪያ አጀንዳ ለመሆን አልበቃም፡፡ ተቋሙንና ኮሚሽኑን ለማቋቋም በነበረው የህግ ማውጣት ሂደት እንደዚሁ ሁለቱም አካላት በክልሎች ላይ የሚኖራቸው ስልጣን ህገ-መንግስታዊነትና ተግባራዊነት በተመለከተ ህገ-መንግስቱን ተንተርሶ የተሰጠ ትንተና ሆነ ምክንያት አልነበረም፡፡

ከላይ እንደተጠቆመው የሁለቱም ተቋማት ማቋቋሚያ አዋጆች በክልል መንግስት ስራ አስፈጻሚ አካላትና ባለስልጣናት የሚፈፀሙ የአስተዳደር ጥፋቶችና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች በተቋሙና በኮሚሽኑ የስልጣን ክልል ስር እንደሚወድቁ ደንግገዋል፡፡   በዚህ ረገድ የተፈጠረው የተሳሳተ ግንዛቤ ምንጩ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀፅ 55 ንኡስ አንቀፅ 14 እና 15 ንባብ ስለመሆኑ አያጠራጥርም፡፡ ሁለቱም አንቀጾች የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንና ተግባር በሚዘረዝረው የህገ መንግስቱ አንቀፅ 55 ውስጥ የሚገኙ ሲሆን ምክር ቤቱ የሠብዓዊ መብት ኮሚሽንንና የእንባ ጠባቂ ተቋምን እንደሚያቋቁም ብሎም ስልጣንና ተግባራቸውን በህግ እንደሚወሰን በማያሻማ አነጋገር ይደነገጋሉ፡፡

የአንቀጽ 55/14/ እና /15/ ድንጋጌዎችን ላይ ላዩን ለሚያነብ ሰው ሁለቱም ተቋማት በፌደራል መንግስት ስልጣን ስር እንደሚካተቱ የተሳሳተ ድምዳሜ ላይ ሊደርስ ይችላል፡፡ የሁለቱም ተቋም ማቋቋሚያ አዋጆች በሚረቀቁበት ወቅት ተቋማቱን አስመልክቶ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የህግና አስተዳደር ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ በቀረበ አንድ ሪፖርት ላይ ተቋማቱ በክልሎች ላይ ስልጣን ሊኖራቸው እንደሚገባ ለማሳመን የህገ-መንግስቱ አንቀፅ 55 /14/እና /15/ ተጠቅሰዋል፡፡ ስለሆነም በዚህ ረገድ ያለውን የተሳሳተ ግንዛቤ ማጥራት ያስፈልጋል፡፡

የእንባ ጠባቂ በየአገራቱ ዝብርቅርቅ መልክና ቅርጽ አለው፡፡ ሆኖም ከሚቋቋምበት መንገድ አንጻር ሲታይ በአንድ መንግስታዊ ተቋም ስር (ለምሳሌ የዩኒቨርስቲ[1] እና የማረሚያ ቤት እንባጠባቂ[2])፣ በግሉ ዘርፍ (ለምሳሌ የባንኮች፣ የኃይል አቅርቦት፣ የኢንሹራንስ፣ የቴሌኮሙኒኬሽን እንባጠባቂዎች[3]) እንዲሁም በጣም በሚታወቅበት መልኩ በአገር አቀፍ፣ በክልሎች፣ ግዛቶችና መስተዳድሮች ደረጃ ይቋቋማል፡፡

በግሉ ዘርፍ እና በተቋም ደረጃ የሚገኘውን ትተን በአገር ዓቀፍ ደረጃ የሚቋቋመውን እንባ ጠባቂ በጥቅል ስንመለከት የሚቋቋምበት መንገድ ሁለት ነው፡፡ ይኸውም አንደኛ አገሪቱ ባጸደቀችው ህገ መንግስት በግልጽ ዕውቅና የተሰጠው ሊሆን ይችላል፡፡ ሁለተኛ በህገ መንግስት ላይ በግልጽ ሳይካተት ፓርላማ በሚያወጣው ልዩ ህግ ሊቋቋም ይችላል፡፡ የተቋሙ የህልውና መሰረት ህገ መንግስት መሆኑ/አለመሆኑ አንድ መሰረታዊ ቁምነ ነገር ያስጨብጠናል፡፡ ይኸውም ህገ መንግስታዊ ዕውቅና ያለው እንባ ጠባቂ ተቋም የመቋቋሙ ዕጣ ፈንታ ለህግ አውጪው የተተወ አይደለም፡፡ ህግ አውጪው መዋቅርና አደረጃጀቱን በልዩ ህግ በመወሰን ተቋሙን የመመስረት ህጋዊ ግዴታ አለበት፡፡ በተቃራኒው የአንድ አገር ህገ መንግስት ስለተቋሙ በግልጽ ካልደነገገ እንደ ህግ አውጪው ፈቃድ እንባ ጠባቂ ሊኖርም ላይኖርም ይችላል፡፡ ህልውና የሚያገኘው አስፈላጊነቱና ጠቃሚነቱ ከታመነበት ብቻ ነው፡፡

የእንባ ጠባቂ ጽንሰ ሀሳብ በአጭር ጊዜ ውስጥ ፈጣን ዕድገት በማሳየት ከሞላ ጎደል በሁሉም የዓለማችንን አገራት ሰፊ ተቀባይነት አግኝቷል፡፡ ተቋሙ የመንግስትን ተጠያቂነት በማረጋገጥ ብሎም አስተዳደራዊ ፍትሕ በማስፈን ሊጫወት የሚችለው ዴሞክራሲያዊና ህገ መንግስታዊ ሚና መሰረታዊ ጥያቄ ባይነሳበትም የተወሰኑ አገራት እጃቸውን ዘርግተው አልተቀበሉትም፡፡ ሌሎች ደግሞ ትልቅ ቦታ ከመስጠታቸው የተነሳ ህልውናው በየምርጫ ዘመን በሚቀያየር ፓርላማ ላይ ጥገኛ እንዳይሆን በማሰብ ጠንካራ ህገ መንግስታዊ መሰረት እንዲኖረው አድርገውታል፡፡ የተቀሩት ደግሞ ህገ መንግታዊ ዕውቅና እስከ መስጠት ደረጃ ባይደርሱም በልዩ ህግ በማቋቋም ህልውና እና ዕውቅና ሰጥተውታል፡፡ ስለሆነም ሲፈለግ ይኖራል፤ ከገዜ በኋላ ካልተፈለገ ይቀራል፡፡

አልባኒያ the People’s Advocate በመባል የሚጠራውን እንባ ጠባቂ ተቋም እ.ኤ.አ በ1998 ዓ.ም. ባጸደቀችው ህገ መንግስት ላይ የማቋቋሚያውን መሰረት ከጣለች በኋላ በቀጣዩ ዓመት በይፋ ህግ እንዲቋቋም አድርጋለች፡፡[4] ሆኖም የኦስትሪያ እንባ ጠባቂ ቦርድ ህገ መንግስታዊ መሰረት ስላልነበረው ተቋሙን የማቋቋም ሀሳብ መጀመሪያ ተቀባይነት ሳያገኝ ከጊዜ በኋላ በህግ ሊቋቋም ችሏል፡፡ የህጉ ረቂቅ ለፓርላማ የቀረበው እ.ኤ.አ በ1972 ዓ.ም. ሲሆን ከሶስት ዓመታት በኋላ ተቀባይነት ሳያገኝ በመቅረቱ ውድቅ ተደርጓል፡፡ ሆኖም ከዚሁ ረቀቂ ይዘትና መንፈስ በመነሳት በድጋሚ የቀረበው ረቂቅ እ.ኤ.አ በ1977 ተቀባይነት አግኝቶ ቦርዱ ሊቋቋም ችሏል፡፡[5] በአሜሪካ የፌደራል እንባ ጠባቂ የሚባል ተቋም የለም፡፡ ኮንግረስ ስራ አስፈጻሚውን መቆጣጠር ለራሱ ብቻ የተተወ ህገ መንግስታዊ ሚና እንደሆነ ጠንካራ አቋም በመያዙ ይህን ታሪካዊ ስልጣኑን አሳልፎ መስጠት አልፈቀደም፡፡[6] የዚህ አመለካከት ተጽዕኖ ተቋሙ ከጥቂት ግዛቶች[7] በስተቀር በአብዛኞቹ ተቀባይነት እንዳያገኝ ምክንያት ሆኗል፡፡

ወደ አገራችን ስንመጣ ሁለቱም ተቋማት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 55/14/ እና /15/ ላይ መሰረታቸው ተጥሏል፡፡ የተወካዮች ምክር ቤት ስልጣንና ተግባራቸውን በዝርዝር ህግ ከመወሰን ውጪ አስፈላጊነታቸውን ጥያቄ የሚያነሳበት ጉዳይ አይደለም፡፡ ሁለቱም ድንጋጌዎች በግልጽ የሚናገሩት ምክር ቤቱ ተቋማቱ ህጋዊ ሰውነት አግኝተው ስራቸውን እንዲያከናውኑ የማድረግ ህገ መንግስታዊ ግዴታ እንዳለበት ነው፡፡ ይሄ ግዴታ በሌሎች ሶስት ህግ መንግስታዊ መሰረት ባላቸው ተቋማትም ላይ ተፈጻሚነት አለው፡፡ በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት ከአንቀጽ 111-113 ድረስ የተጠቀሱት የዋና ኦዲተር መስሪያ ቤት፣ ብሔራዊ የምርጫ ቦርድ እና የህዝብ ቆጠራ ኮሚሽን እንደ እንባ ጠባቂ ሁሉ ህገ መንግስታዊ ናቸው፡፡

የድንጋጌዎቹን ይዘት ከፌደራላዊ የስልጣን ክፍፍል ጋር ማምታታት የፌደራላዚም ስርዓት ሀሁ ግንዛቤ የማጣት ያክል ነው፡፡ የአንቀጽ 55 ርዕስ ‘ስልጣንና ተግባር’ ስለሚል ብቻ ሁለቱም ተቋማት በፌደራል መንግስት የስልጣን ክልል ስር እንደሆኑ ማሰብ ትርጉም አለመስጠቱ ብቻ ሳይሆን ፌደራሊዝምን በአሀዳዊነት መነጽር የማየት ችግር ያንጸባርቃል፡፡

ለመሆኑ ‘እንባ ጠባቂ ተቋም እና የሰብዓዊ መብት ኮሚሽን በፌደራል መንግስት ስልጣን ስር ናቸው ማለት ምን ማለት ነው?’ በፌደራል እና ክልል ስልጣን (jurisdiction)[8] ስር የሚወድቁ ጉዳዮች በአንቀጽ 51 እና 52 ስር ተለይተው ተዘርዝረዋል፡፡ ዝርዝሮቹ በሙሉ የሚናገሩት በማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ዘርፍ ስር ስላሉ ጉዳዮች ነው፡፡ ስልጣን በፌደራል እና በክልል የሚከፋፈለው አንድ ተቋም በሚያከናውነው ጉዳይ እንጂ ተቋሙን ራሱን የፌደራል/የክልል በማለት አይደለም፡፡ ለዚህም ነው እንባ ጠባቂ የፌደራል ብቻ ነው የሚል አነጋገር ትርጉም የማይሰጠው፡፡

ህገ መንግስቱ የክልል መንግስታት የራሳቸውን እንባ ጠባቂና ሰብዓዊ መብት ኮሚሽን እንደሚያቋቁሙ ሳይናገር በዝምታ ማለፉ ተገቢና ትክክል ነው፡፡ ምክንያቱም ውሳኔው ከመነሻው የክልሎቹ የራሳቸው ነው መሆን ያለበት፡፡ ሲፈልጉ በህገ መንግስታቸው ለተቋማቱ ዕውቅና መስጠት ይችላሉ፡፡ አሊያም ደግሞ በህገ መንግስታቸው ውስጥ ማካተቱን ትተው አስፈላጊ ሆኖ ባገኙት ጊዜ ህግ አውጥተው ማቋቋም (አሊያም እስከነጭራሹ አለማቋቋም) ይችላሉ፡፡

ሲጠቃለል የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ህገ መንግስት አንቀጽ 55 /14/ እና /15/ ድንጋጌዎች ይዘት የፌደራሉ እንባ ጠባቂ ህገ መንግስታዊ እንደሆነና የተወካዮች ምክር ቤት በዝርዝር ህግ ስልጣንና ተግባሩን በመወሰን ህጋዊ ሰውነት ኖሮት እንዲቋቋም የማድረግ ህገ መንግስታዊ ግዴታ እንዳለበት ነው፡፡ ስለሆነም ሁለቱም ተቋማት በክልል መንግስታት ስራ አስፈጻሚ ላይ ስልጣን እንዳላቸው ከድንጋጌዎቹ በመነሳት የሚቀርብ ክርክር ፈር የሳተና የፌደራል ስርዓት ከሚያስነሳቸው ዘርፈ ብዙ ጭብጦች ውስጥ ሊካተት የማይችል፣ ጥልቀት ያነሰው፣ ‘ከላይ-በላይ ንባብ’ የሚመነጭ ክርክር ነው፡፡ ብዙ ባያስኬድም ከስልጣን ክፍፍል አንጻር ክርክር ከቀረበ መቅረብ ያለበት ተቋማቱ ከፌደራልና ከክልል በየትኛው ስልጣን ስር እንደሚወድቁ በመጠየቅ ሳይሆን ተቋማቱ የሚያከናውኑት ጉዳይ በማን ስልጣን ስር እንደሆነ ጥያቄ በማንሳት ነው፡፡ ስለሆነም ጥያቄው የሚከተለውን መልክ ይይዛል፡፡ ‘የክልል ስራ አስፈጻሚ አካላትንና ባለስልጣናትን ተጠያቂነት ማረጋገጥ፣ በክልሉ አስተዳደራዊ ፍትሕ ማስፈን፣ ለአስተዳደራዊ በደሎች መፍትሔ መስጠት፣ አስተዳደራዊ ጥፋትን የማረም ስልጣኑ የማን ነው? የራሱ የክልሉ ነው? ወይስ የፌደራል መንግስት? በክልል ጉዳይ የሚያገባው ማነው? የፌደራል ወይስ የክልሉ መንግስት?’

የጥያቄዎቹ ቀላልነት ሲታይ ምላሽ መስጠት መሰረታዊ ባልሆነ ጉዳይ መባከን ተደርጎ ሊቆጠር ይችላል፡፡ ይሁን እንጂ ከ500 በላይ አባላት ያቀፈ ፓርላማ ጥያቄውን በወጉ መመለስ ተስኖት ‘ፈተናውን የወደቀ’ እንደመሆኑ በቂ ማብራሪያ መስጠት ግድ ይላል፡፡

[1] ለበለጠ ግንዛቤ Mundinger, Donald C. 1967. “The University Ombudsman: His Place on the Campus.” The Journal of Higher Education (Ohio State University Press) 493-499. Accessed June 27, 2014. http://www.jstor.org/stable/1980338. ይመለከቷል፡፡

[2] ለበለጠ ግንዛቤ Fulmer, Richard H. 1981. “The Prison Ombudsman.” Social Service Review (The University of Chicago Press) 55: 300-313. Accessed June 27, 2014. http://www.jstor.org/stable/30011474. ይመለከቷል፡፡

[3] Trevor Buck, Richard Kirkham and Brian Thompson, The Ombudsman enterprise and administrative Justice. (ashgate publishing company፣ 2011) ገፅ 7

[4] Joachim Stern, Albania. In G. Kucsko-Stadlmayer (Ed.), European Ombudsman-Institutions A comparative legal analysis regarding the multifaceted realisation of an idea. (SpringerWienNewYork, 2008) ገፅ 70

[5] Brigitte Kofler, Austria. In G. Kucsko-Stadlmayer (Ed.), European Ombudsman-Institutions A comparative legal analysis regarding the multifaceted realisation of an idea. (SpringerWienNewYork, 2008) ገፅ 90

[6] Kass, Benny L. 1967. “We Can, Indeed, Fight City Hall: The Office and Concept of Ombudsman.” American Bar Association Journal (American Bar Association) 53 (3): 231-236. Accessed June 28, 2104. http://www.jstor.org/stable/25723944.

[7] ለምሳሌ ሀዋይ፣ ኔብራስካ፣ አዮዋ፣ አላስካና አሪዞና የእንባ ጠባቂ ተቋም በህግ አቋቁመዋል፡፡ Hill, Larry B. 2002. “The Ombudsman Revisited: Thirty Years of Hawaiian Experience.” Public Administration Review (Wiley/American Society for Public Administration) 61: 24-41. Accessed June 27, 2014. http://www.jstor.org/stable/3110280.

[8] ምንም እንኳን በኢ.ፌ.ዲሪ. ህገ መንግስት አንቀጽ 51 እና 52 የእንግሊዝኛ ቅጂ ርዕሶች ላይ ህግ አውጪው የተጠቀመው powers and duties የሚል ቢሆንም የስልጣን ክልልን ወይም ወሰንን በአግባቡ የሚገልጸው ቃል jurisdiction ነው፡፡

Federations and Second Chambers

Federations and Second Chambers

[Taken from   FEDERALIAM TEACHING MATERIAL( JLSRI)  by Dr. Assefa Fissha]

…It  is  argued  that  a  second chamber based on a different composition and representing the interests of states, more specifically  less populous states, is an  institution that reflects the normative diversity  inherent  in  federalism.  It  is  also suggested  that  second  chambers reflecting  the  entrenched  representation  of  the  states  distinguishes  federations from  other  types  of  polities.  This  chapter,  comparative  in  its  approach, commences by considering  the underlying  rationale  for having second chambers and then proceeds to their manner of composition, election and more importantly,
the powers entrusted upon them by their respective constitutions. The main point that the author develops is the idea that the Ethiopian Constitution, by establishing a  non-legislative  upper  house,  runs  the  risk  of  concentration  of  power  at  the center, to the exclusion of the states, and consequently leaves the states alone. The Constitution fails to ensure the constituent units‟ proper place in the institutions of power sharing as well as  in  the process of policy-making at  federal  level and  by doing so it betrays the federal idea significantly..

READ FULL TEXT OF Federations and Second Chambers

READ FULL TEXT OF FEDERALISM TEACHING MATERIAL