Tag: case brief

የህግ ትርጉም መለወጥ እና ተለውጧል ስለሚባልበት ሁኔታ

የህግ ትርጉም መለወጥ

የህግ ትርጉም አስገዳጅነቱ ለስር ፍ/ቤቶች እንጂ ለራሱ ለችሎቱ አይደለም፡፡ ችሎቱ በሌላ ጊዜ በተመሳሳይ ጭብጥ የተለየ አቋም ሊይዝ ይችላል፡፡ የትርጉም መለወጥ በጠባቡ ካልተተገበረ በስር ፍርድ ቤቶች ዘንድ ሊኖረው የሚገባውን የተሰሚነትና የተቀባይነት ደረጃ በእጅጉ ያሳንሰዋል፡፡ መረሳት የሌለበት ነገር ወጥነት ለበታች ፍ/ቤቶች ብቻ ሳይሆን ለራሱ ለችሎቱም በእጅጉ ያስፈልገዋል፡፡ በአንድ ጭብጥ ላይ በየጊዜው የሚቀያየር የህግ ትርጉም ተቀባይነቱ አጠያያቂ ነው፡፡ ወዲያው ወዲያው አቋም ሲለዋወጥ ፍርድ ቤቶችን ያደናግራል፡፡ Continue reading “የህግ ትርጉም መለወጥ እና ተለውጧል ስለሚባልበት ሁኔታ”