አዋጅ ቁጥር 684-2002 የተሻሻለው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ማቋቋሚያ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር 684/2002

የተሻሻለው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ማቋቋሚያ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት ነጻ የዳኝነት አካል የተቋቋመ በመሆኑ፤ ይህ ነፃ የዳኝነት አካል ነፃነቱ የሚረጋገጠው ተቋማዊ እና ዳኝነታዊ ነፃነቱን መጠበቅ ሲቻል በመሆኑ፤ ይህንንም ለማድረግ ፍርድ ቤቶች ከማናቸውም አካል ተፅዕኖ ነፃ ሆነው ራሳቸውን ማስተዳደር መቻል ያለባቸው በመሆኑ፤  የፌዴራል ፍርድ ቤቶች ዳኞችን ተጠያቂነት ማስፈንና የጉባዔውን አባላት ስብጥር ማስፋት በማስፈለጉ፤ ለዚህም አስፈላጊውን መዋቅር ያሟላና ሥልጣኑ በህግ እውቅና የተሰጠው የዳኝነት አስተዳደር አካል ማቋቋም አስፈላጊ ሆኖ ስለተገኘ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 ንዑስ አንቀጽ /1/ መሠረት የሚከተለው ታውጇል። Continue reading “አዋጅ ቁጥር 684-2002 የተሻሻለው የፌዴራል ዳኞች አስተዳደር ማቋቋሚያ አዋጅ”

አዋጅ ቁጥር 322-1995 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በተወሰኑ ክልሎች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር 322/1995

የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በተወሰኑ ክልሎች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 78(2) የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አስፈላጊ ሆኖ ሲያገኘው የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሆነ የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት በሀገሪቱ በሙሉ ወይም በከፊል እንዲደራጅ በሁለት ሦስተኛ ድምጽ ሊወስን እንደሚችል በመደንገጉ፤ በተወሰኑ ክልሎች የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን ማደራጀት በማስፈለጉ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ-መንግሥት አንቀጽ 78(2) እና አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ Continue reading “አዋጅ ቁጥር 322-1995 የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤትን በተወሰኑ ክልሎች ለማደራጀት የወጣ አዋጅ”

አዋጅ ቁጥር 188-1992 የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የወጣ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር 188/1992

የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የወጣ አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገመንግሥት በአንቀጽ 34 ንዑስ አንቀጽ 5 መሠረት የጋብቻ፣ የግልና የቤተሰብ መብት ላይ የሚነሱ የሕግ ጉዳዮችን አስመልክቶ በፈቃደኝነት ላይ በተመሰረተ ሁኔታ በባህላዊና በሃይማኖት ሕጐች ለመዳኘት የሚቻል በመሆኑ፤ በሕገ መንግሥቱ አንቀጽ 78 ንዑስ አንቀጽ (5) መሠረት የባሕልና የሃይማኖት ሕጐችን መሠረት አድርገው የሚዳኙ ሃይማኖታዊና ባህላዊ የፍርድ ተቋማት በሌሉ ጊዜ የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤትና የክልል ምክር ቤቶች እነዚህን ተቋማት እንደአስፈላጊነቱ እንዲያቋቁሙ ሥልጣን የተሰጠ በመሆኑ፤ ከሕገ መንግሥቱ መጽደቅ በፊት በሥራ ላይ የነበሩና የመንግሥት ዕውቅና የነበራቸው ሃይማኖታዊና ባህላዊ የፍርድ ተቋማት ሕገ መንግሥቱ በሚሰጠው ዕውቅና መሠረት በአዲስ መልክ ሊደራጁ እንደሚችሉ በተደነገገው መሠረት፤ ቀደም ሲል ከግማሽ ምዕተ ዓመት በላይ ተቋቁመው አንዳችም የማሻሻያ ለውጥ ሳይደረግባቸው ባሉበት ሁኔታ እንዲቆዩ የተደረጉትን የሸሪዓ ፍርድ ቤቶች አቋም ብቃት ባለው ሁኔታ እንዲደራጁ ማድረግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት አንቀጽ 55 (1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡ Continue reading “አዋጅ ቁጥር 188-1992 የፌዴራል ሸሪዓ ፍርድ ቤቶችን አቋም ለማጠናከር የወጣ አዋጅ”

አዋጅ ቁጥር 25-1988 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ

አዋጅ ቁጥር 25/1988 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የዳኝነት ሥልጣን በፌዴራል መንግሥቱና በክልሎች የተከፋፈለ በመሆኑ፤ ሕገ መንግሥቱን መሠረት በማድረግ የፌዴራል ፍርድ ቤቶችን ሥልጣን መወሰን አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፤ በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገ መንግሥት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል። Continue reading “አዋጅ ቁጥር 25-1988 የፌዴራል ፍርድ ቤቶች አዋጅ”