የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽን ማቋቋምያ /ረቂቅ/ አዋጅ

                     አዋጀ ቁጥር —–/2011

              ዕርቀሰላም ኮሚሽን ማቋቋምያ /ረቂቅ/ አዋጅ    

በኢትዮጵያ ለበርካታ ዓመታት በተለያዪ ማህበረሰባዊ እና ፖለቲካዊ ግጭቶች ምክንያት በህዝቦች መካከል የተደራረቡ የቁርሾ ስሜቶችን ለማከም እውነትና ፍትህ ላይ መሰረት ያደረገ እርቅ ማውረድ አስፈላጊ በመሆኑ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግሥት እንዲሁም ኢትዮጵያ በተቀበለቻቸው ዓለም አቀፍና አሕጉራዊ ስምምነቶች የተረጋገጡትን መሰረታዊ የሰብዓዊ  መብቶች ሳይሸራረፉ እንዲከበሩ እና ተግባራዊ ለማድረግ በተደጋጋሚ የተከሰቱ ጉልህ የመብት ጥሰቶችን ምንነት በግልጽ መለየት አስፈላጊ ስለሆነ እና ለእርቀ ሰላሙም አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ፤

በተለያዩ ጊዜዎቸ እና የታሪክ አጋጣሚዎች የሰብዓዊ መብት ጥሰት እና ሌላ በደል ተጠቂዎች የሆኑ ወይም ተጠቂዎች ነን ብለው የሚያምኑ ዜጎች  በደላቸውን የሚናገሩበትና በደል ያደረሱ ዜጎች ላደረሱት በደል በግልፅ በማዉጣት የሚፀፀጡበት እና ይቅርታ የሚጠይቁበት  መንገድ በማበጀት እና እርቀ ሰላም በማዉረድ ዘላቂ ሰላም ለማስፈን አስፈላጊ መሆኑ ስለታመነበት ፤

ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ፣ እየፈረሰ የሚሰራ ሳይሆን እየተገነባ የሚሄድ ስርዓት ለመፍጠር፣  ዲሞክራሲያዊ ሀገርና ማህበረሰብ ለመገንባት ሰፊና ተቀባይነት ያለው የእውነትና፣የእርቅ እና የሰላም ዓላማ ያነገበ፣ለግጭትና ቁርሾ ምክንያት የሆኑትን ዝንፈቶች ምክንያቶችና የስፋት መጠን አጣርቶ እውነታውን በማዉጣት ተመልሰው እንዳይመጡ በዘላቂነት ለመፍታት የሚያስችሉ  ተግባራዊ እርምጃዎችን የሚወስድና እና የመፍትሄ አቅጣጫዎችን የሚያመነጭ  ገለልተኛ እና ነጻ ኮሚሽን ማቋቋም በማስፈለጉ፤

በኢትዮጵያ ፌደራላዊ ዲሞክራስያዊ ሪፐብሊክ ሕገ መንግስት አንቀፅ 55 /1/ መሠረት የሚከተለው ታዉጇል

 1. አጭር ርዕስ

ይህ አዋጅ “የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅ ቁጥር _________/2011” ተብሎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡

 1. መቋቋም

1/ የዕርቀ-ሰላም ኮሚሽን (ከዚህ በኋላ ኮሚሽን እየተባለ የሚጠራ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል።

2/    ኮሚሽኑ የራሱ ጽሕፈት ቤት ፣በጀት እና አስፈላጊ የሆኑ ሠራተኞች ይኖሩታል፡፡

3/    የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት ሕጋዊ ሰዉነት አለው፡፡

4/    የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል፡፡

 1. የኮሚሽኑ አባላትና አሰያየም

1/     የኮሚሽኑ አባላት ቁጥር በመንግስት የሚወሰን ይሆናል፡፡

2/     የኮሚሸኑ ሰብሳቢ ፣ምክትል ሰብሳቢ እና ሌሎች አባላት በጠቅላይ ሚኒስቴሩ አቅራቢነት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤቱ ይሰየማሉ::

3/     የጽሕፈት ቤቱ ኃላፊ የኮሚሽኑ ፀሐፊ ሆኖ ያገለግላል::

 1. የኮሚሽኑ ዓላማ

የኮሚሽኑ ዓላማ በኢትዮጵያ ህዝቦች መካከል ሰላም፣ ፍትህ፣ ብሄራዊ አንድነትና መግባባት፣ እንዲሁም እርቅ እንዲሰፍን መስራት ነው፡፡

 1. የኮሚሽኑ ስልጣንና ተግባር

ኮሚሽኑ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

1/    ስራዉን በሚመለከት ማንኛዉም ያገባኛል የሚል ሰው ወይም አካል ሃሳቡ እንዲያቀርብ ጥሪ ማቅረብ እና አስፈላጊውን ምዝገባ ማካሄድ፤

2/    ስራዉን በቴክኖሎጂ የተደገፈ በማድረግ ተደራሽ፣ አሳታፊ፣ ሁሉም አካል እኩል ተደማጭ የሚሆንበት የዕርቀ-ሰላም ውይይት መድረክ ማዘጋጀት፤

3/    የተለያየ ዐቋም የያዙ የህብረተሰብ ክፍሎችን በማወያየትና ለሃገራዊ እርቅ መሰረት የሚሆኑ የጋራ መርህዎችንና እሴቶችን መለየት፤

4/    የግጭቶችንና የመብት ጥሰቶቹን መነሻ ምክንያት ለመለየት፣ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አውዶችን፣ የተጎጂዎችንና ጥፋተኞቸን አስተያየት በመወሰድ ምርመራ ማካሄድ፤

5/    ለሰራው አስፈላጊ ነው ብሎ ያመነበትን ማንኛዉንም የሰነድ ወይም ሌላ መረጃ ከመንግስትም ይሁን ከማናቸውም ሌላ አካላት የመቀበልና በፈለገው ጊዜ እንዲያቀርቡ የማዘዝ፤

6/    ሀላፊነቱን ለመወጣት የማናቸውንም ተቋም ይዞታ የመጎብኘት፣ በጉብኝቱም ጊዜ የሚያገኛቸውን ማናቸውንም መረጃዎችና፣ ሰነዶችን ቅጂ የመውስድ፤

7/    መረጃ ለመሰብሰብ በተናጠልም ሆነ በቡድን፣ በምስጢርም ሆነ ለሀዝብ ክፍት በሆነ ሁኔታ ቃለ መጠይቅ ማድረግ፣ መጥሪያ በመላክ ማንኛዉም ሰው  እንዲቅርብ የማዘዝ እና ቃሉን በቃለ መሃላ እንዲሰጥ የማድረግ፤

8/    ሃላፊነቱን ለመወጣት እንድሁኔታው የፌደራልም ሆነ የክልል  ፖሊስ እገዛ የማግኘት፤

9/    በምርመራው የሚደርስባቸውን መደምደሚያዎች እንደሁኔታው በየጊዜው ለህዘብና ለሚመለክታቸው የመንግስት አካላት ማሳወቅ፤እና

10/   በህዝቦች መካከል የተፈጠረ ልዩነት እንዲረግብ እና መግባባት እንዲፈጠር  እርቀ ሰላም እንዲወርድ የማድረግ።

 1. የኮሚሽኑ ስብሰባ

1/    የኮሚሽኑ መደበኛ ስብሰባ በየአስራ አምስት ቀኑ ይካሄዳል፣ ሆኖም እንደአስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡

2/    ከኮሚሽኑ አባላት  ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከተገኙ ምልዓተ-ጉባኤ ይሆናል፡፡

3/    የኮሚሽኑ ምክረ ሃሳቦች በስምምነት ያልፋሉ፡፡

4/    የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ኮሚሽኑ የራሱን የስብሰባ ሥነ-ሥርዓት ደንብ ሊያወጣ ይችላል፡፡

 1. የኮሚሽኑ ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ:-

1/    ኮሚሽኑን ይመራል

2/    አጠቃላይ የስራ እንቅስቃሴዉን በበላይነት ይመራል

3/    ለኮሚሽኑ አስፈላጊ የሆኑ የድጋፍ ሰጭ ሠራተኞች የምድባል

4/    ኮሚሽኑን በመወከል ከሌሎች አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል

 1. የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር

የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ:-

1/    ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ ሰብሳቢዉን ተክቶ ይሰራል፤

2/    በሰብሳቢው የሚሰጡት ተግባራት የፈጽማል::

 1. የጽሕፈት በቱ አቋም

የኮሚሽኑ ጽሕፈት ቤት:-

1/    በጠቅላይ ሚኒስትሩ የሚሾም ሃላፊና ፤እና

2/    አስፈላጊ ሰራተኞች ይኖሩታል፤

3/    የኮሚሽኑ ዋና ፅ/ቤት በአዲስ አበባ ሆኖ እንደአስፈላጊነቱ በሌሎች የአገሩቱ ክፍሎች ቅርንጫፍ      ሊኖረው ይችላል::

 1. የጽህፈት ቤት ስልጣንና ተግባር

      ጽሕፈት ቤቱ የሚከተሉት ሥልጣንና ተግባራት ይኖሩታል:-

1/    ለኮሚሽኑ አጠቃላይ የአስተዳደርና ፋይናንስ አገልግሎት ይሰጣል፤

2/    ለኮሚሽኑ የህዝብ ተሳትፎና ምክክር መድረኮችን የሎጅስቲክስ ድጋፍ ይሰጣል፤

3/    የኮሚሽኑን ቃለ ጉባኤዎችን፣ ውሳኔዎችንና ሌሎች ሰነዶችን በሚገባ ተመዝግበው እንዲጠበቁ ያደርጋል ፤

4/    የኮሚሽኑን ስራ ለማሳለጥ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል።

 1. ጽህፈት ቤት ሃላፊ ስልጣንና ተግባርና

የጽ/ቤቱ ሃላፊ :-

1/   የጽሕፈት ቤቱ ሥራዎች ይመራል ፣ ያስተዳድራል፤

2/   የኮሚሽኑ ዕቅድና በጀት ያዘጋጃል ሲፀድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፤

3/   ጽሕፈት ቤቱ ከሶስተኛ ወገኖች ጋር በሚያደርጋቸው ግንኙነቶች ጽሕፈት ቤቱን      ይወክላል::

 1. የኮሚሽኑ ገለልተኝነት

ኮሚሽኑ ስራውን በነፃነትና በገለልተኝነት ያከናውናል።

 1. የሰራ ዘመን

1/    የኮሚሽኑ የስራ ዘመን አስከ 3 ዓመት ነው።

2/    በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ 1 የተጠቀሰው ቢኖርም የኮሚሽኑን የስራ ዘመን እንድሁኔታው ሊራዘም ይችላል።

 1. 14. የመተባበር ግዴታ

ማንኛውም ሰው ኮሚሽኑ በዚህ አዋጅ የተሰጠውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ለሚያቀርበው ማንኛውንም ህጋዊ ጥያቄ ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት።

 1. 15. በጀት

የኮሚሽኑ  በጀት በመንግሥት ይመደባል።

 1. 16. የሂሳብ መዛግብት

1/    ኮሚሽኑ የተሟሉና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል፡፡

2/    የኮሚሽኑ የሂሳብ መዛግብትና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም እርሱ በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡

 1. 17. ጠቋሚዎችና ምስክሮችን ስለመጠበቅ

1/    ማንኛዉም ሰው በኮሚሽኑ ፊት ቀርቦ በሚሰጠው ቃል መሰረት ክስ ሊመሰረትበት እንደዚሁም የሰጠው ቃል በእርሱ ላይ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብበት አይችልም፡፡

2/    ለጠቋሚዎችና ለምስክርች ጥበቃ ለማድረግ የወጣ ሕግ ለኮሚሽኑ ቃላቸው እና መረጃ ለሚሰጡ ሰዎችም ተግባራዊ ይሆናል::

 1. 18. አዋጁ የሚጸናበት ጊዜ

ይህ አዋጅ በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ከ ከፀደቀበት ቀን ጀምሮ የጸና ይሆናል።

አዲስ አበባ፤ ህዳር ….. ቀን 2011 ዓ.ም

 

ሳህለወርቅ ዘዉዴ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊዲ ሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዚደንት

Administrative Boundaries and Identity Issues Commission Establishment /Draft/ Proclamation

Proclamation  No …../2018

Administrative Boundaries and Identity Issues Commission Establishment /Draft/ Proclamation

WHEREAS, It is found necessary, by strengthening the federal system to reinforce the underway diversity of nations, nationalities and peoples;

WHEREAS, it is become necessary to solve issues of administrative boundaries, self government and Identity questions that repeatedly occur between regions nationally and for lasting;

WHEREAS, it is realized that controversy relating administrative boundaries is source of conflicts between various nations, nationalities and peoples;

WHEREAS, it is become necessary the need for a neutral, highly professional and peaceful solution to these problems since conflicts with administrative boundaries are a cause of great instability;

NOW, THERFORE, in accordance with Article 55 (1) of the Constitution of the Federal Democratic Republic of Ethiopia, it is hereby proclaimed as follows:

 1. Short Title

This proclamation may be cited as the “Administrative boundaries and Identity issues commission Establishment proclamation No. …../2018”

 1. Definition

1/            “Administrative boundaries” means issues related to self-administration, identity questions and other similar events that rise in relation to administrative issues.

2/“Commission” means the ‘Administrative Boundaries and Identity issues Commission’ established under Article 3 (1) of this Proclamation.

 1. Establishment

1/            Administrative Boundaries Commission (hereinafter referred to as “the Commission”) is hereby establish by this proclamation.

2/            The commission shall have Administrative Boundaries and identity question Commission, its own office and necessary staff.

3/            The commission shall be accountable to the prime Minister.

 1. Objectives

The objectives of the commission shall be to submit recommendation to the Public, the House of the federation, the House of People’s Representatives and the Prime minister through the analysis of causes and causes of administrative boundaries conflicts, self government and identity issues in participatory, explicit, inclusive and scientific manner.

 1. Powers and Duties of the commission

1/            provide alternative recommendations to the House of the Federation and the Prime Minister by studying any problems and conflict that are related to the administrative boundaries demarcation and issues of identity.

2/            Provide recommendations to the House of the Federation on amendments actions that has to be taken to promote and consolidate unity of peoples based on equality and their  mutual consent.

3/            Provide recommendations, for the continued determination and alteration of administrative boundary decisions, to the House of the Federation, to the House of People’s Representatives and to the Prime minister, in order to expand appropriate constitutional principles, transparency and efficient system or amendment of laws.

4/            Present recommendations to the House of the Federation for consideration, where by investigating administrative boundaries controversies which are directed to it from the House of the Federation, the House of Peoples’ Representatives and the Prime minister.

5/            Facilitate ways in which Conflicts arise over administrative boundaries have been resolved, the renewal and strengthen of good relations between neighboring regions.

6/            Provide recommendations to the House of the Federation, the House of People’s Representatives and the Prime minister on the measures that has to be taken to make administrative boundaries is not further cause of conflicts.

7/            Initiate the policy framework of administrative boundaries to make the administrative boundaries and their area of ​​well-being for development and commerce.

8/            Collect public opinion on issues of administrative boundaries.

9/            Collect opinion and inputs for the study from regional and federal officials, political parties, and other stakeholders.

10/         Prepare strategy and detailed plan that show the process of gathering public input and feedback, which ensures that the process includes all sections of the community.

 1. Administrative boundaries and identity Issues

Any administrative boundaries decision and identity question shall be studied by the commission and resolved by House of the Federation in accordance with applicable laws.

 1. Appointment of the members of the commission

1/            Number of members of the commission shall be determined by the government.

2/            Individuals designated as members of the Commission shall have community commendation and good reputation for their ethical conduct, educational preparation, and work experience.

3/            The Chairperson of the Commission and the Deputy Chairperson and other members of the Commission shall, up on recommendation by the Prime Minister and appointed by the House of Peoples’ Representatives of the Federal Democratic Republic of Ethiopia.

 1. Meetings of the commission

1/            The Commission shall hold its regular meetings every fifteen days; provided, however that it may hold extraordinary meetings at any time where necessary.

2/            There shall be quorum where more than half of the members of the commission are present at a meeting.

3/            The Council shall pass its recommendation by consensus.

4/            without prejudice to the provisions of this Article, the Commission may adopt its own rules of procedure.

 1. Powers and Duties of the chairperson of the commission

Chairperson of the commission shall:

1/            Direct the general activities of the commission;

2/              Assign the necessary supportive staff to the commission; and

3/            Make relation with third parties representing the commission.

 1. Powers and Duties of the deputy chairperson of the commission

The deputy chairperson of the commission shall:

1/            perform the activity of the chairperson in his absence.

2/            perform other activity given to him by the chairperson

 1. Office of the Commission

1/            The head of Office of the Commission shall be appointed by the Government and shall manage the Office’s staff and resources.

2/            Direct the secretarial and logistic support to members of the Commission

 1. Powers and Duties of Office of the Commission

The Office of the commission shall:

1/            Provide general administrative and financial services to the Commission;

2/            Provide research and study services to the Commission;

3/            Provide logistical support to the Commission’s public participation and consultation forums;

4/            It shall compile the minutes of the commission, decisions and documents of the commission;

5/            Provide the necessary support and assistance to facilitate the work of the commission.

 1. Powers and Duties of the Head of the office

The Head of the office shall:

1/               Direct and administer the activities of the office.

2/               Prepare the work programs and budgets of the commission and implement same upon approval;

3/              Represent the Office in all dealings with third parties.

 1. The neutrality of the Commission

The Commission undertakes the work independently and impartially.

 1. Terms of office

1/            The term of the office of Members of the Commission shall be 3 years.

2/            Notwithstanding the provision of sub-article (1) of this article the House of Peoples Representative shall extend terms of the office of Members of the Commission.

 1. Duty to Cooperate

Any person shall have an obligation to cooperate with the Commission when he requested any legal questions where the Commission, according to this proclamation, has been doing its functions.

 1. Protection of Witnesses and whistle-blower

1/            No one may be accused by the testimony given to the commission as well as the    testimony given before the commission could not serve as and evidence up on him;

2/            The provisions of the laws for the protection of the witnesses and whistleblowers shall apply to those who have provided testimonies and evidences to the Commission

 1. Budget

The budget of the Commission shall be allocated by the government.

 1. Books of Account

1/            The office of the commission shall keep complete and accurate books of accounts.

2/            The books of accounts and financial documents of the Office shall be audited annually by the Federal General Auditor or by Auditor designated by him.

 1. Powers to Issue Regulations and Directives

1/ The Council of Ministers may issue regulations necessary for the implementation of this Proclamation

2/ The Commission may issue directives for the implementation of this proclamation and regulations issued pursuant to sub-article (1) of this Article.

 1. Effective Date

This proclamation shall come into force upon the date of approving by the House of Peoples’ Representatives.

Addis Ababa

                                       date ———- year

                                                SAHLEWORK ZEWDE

PRESIDENT OF THE FEDERAL DIMOCRATIC REPUBLIC OF ETHIOPIA

 

 

የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋም የወጣ /ረቂቅ/ አዋጅ

አዋጅ ቁጥር —–/2011

አስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽንን ለማቋቋየወጣ አዋጅ

የፌዴራል ስርዓቱን በማጠናከር እየተገነባ የመጣውን የብሔር ብሔረሰብ እና ህዝብ ብዝሃነት ማጎልበት አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በክልሎች የአስተዳደር ወሰን፣ ራስን በራስ ማስተዳደርና በማንነት ጥያቄዎች ዙርያ በተደጋጋሚ የሚታዩ ችግሮችን አገራዊ በሆነና በማያዳግም መንገድ መፍታት በማስፈለጉ፣

ከአስተዳደር ወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሱ ውዝግቦች በተለያዩ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ህዝቦች መሃል የቅራኔ ምንጭ መሆናቸውን በመገንዘብ፣

ከአስተዳደር ወሰን ጋር ተያይዞ የሚነሱ ግጭቶች ከፍተኛ ለሆነ አለመረጋጋት መንስዔ በመሆናቸው፣ ለነዚህ ችግሮች ገለልተኛ በሆነ፣ ከፍተኛ ሞያዊ ብቃት ባለውና ሰላማዊ በሆነ መንገድ መፍትሄ ማፈላለግ አስፈላጊ ሆኖ በመገኘቱ፣

በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ህገመንግስት አንቀጽ 55(1) መሠረት የሚከተለው ታውጇል፡፡

 1. አጭር ርዕስ

ይህ አዋጅ‹‹ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን ማቋቋሚያ አዋጅቁጥር ——–/2ዐ11›› ተብሎሊጠቀስይችላል፡፡

 1. ትርጓሜ

1/     “የአስተዳደር ወሰን” ማለት ራስን በራስ ማስተዳደር ፣ ከማንነት ጥያቄ እና ከሌሎች ተመሳሳይ ክስተቶች ጋር በተያይዘ የሚነሱ የወሰን ጉዳዮች ነው

2/     “ኮሚሽን” ማለት በዚህ አዋጅ አንቀፅ 3(1) መሰረት የተቋቋመ የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጥያቄ ጉዳዮች ኮሚሽን ነው፡፡

 1. መቋቋም

1/    የአስተዳደር ወሰን እና የማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን (ከዚህ በኋላ ‘ኮሚሽን’ እየተባለ የሚጠራ) በዚህ አዋጅ ተቋቁሟል።

2/    ኮሚሽኑ የአስተዳደር ወሰን፣ ራስን በራስ ማስተዳደር  እና ማንነት ጉዳዮች ኮሚሽን፣ ጽህፈት ቤት እና   አስፈላጊ ሰራተኞች፣ ይኖሩታል፡፡

3/    የኮሚሽኑ ተጠሪነት ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሆናል፡፡

 1. የኮሚሽኑ ዓላማ

ኮሚሽኑ አሳታፊ፣ ግልጽ፣ አካታችና ሳይንሳዊ በሆነ መንገድ ከአስተዳደር ወሰኖች፣ ራስን በራስ ማስተዳደር  እና ከማንነት ጋር የተያይዙ ግጭቶችንና መንስኤያቸውን በመተንተን የመፍትሄ ሃሳቦችን ለህዝብ፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  እና ለአስፈጻሚው አካል  ማቅረብ ነው።

 1. የኮሚሽኑ ሥልጣንና ተግባር

ኮሚሽኑ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

1/    ከአስተዳደራዊ ወሰኖች አከላለል፣ ራስን በራስ ማስተዳደር እንዲሁም ከማንነት ጥያቄ ጋር የተገናኙ ማናቸውንም ችግሮችንና ግጭቶችን በጥናት ለይቶ አማራጭ የመፍትሄ ሃሳቦችን ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት  ሪፖርት ያቀርባል፤

2/    በህዝቦች እኩልነትና ፈቃድ ላይ የተመሰረት አንድነት ስር እንዲሰድና እንዲዳብር ለማድረግ ሊወሰዱ ስለሚገባቸው እርምጃዎች ማሻሻያ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ምክረ ሃሳቦችን ያቀርባል፤

3/    አስተዳደራዊ ወሰኖች በቀጣይነት የሚወሰኑበትንና የሚለወጡበትን መንገድ በተመለከት አግባብነት ያላቸውን ህገ-መንግስታዊ መርህዎች ያገናዘበ፣ ግልጽና ቀልጣፋ ስርዓትወይም የህግ ማሻሻያ እንዲዘረጋ ጥናት በማድረግ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ለፌዴሬሽን ምክር ቤት እና ህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ምክረ ሃሳብ ያቀርባል፤

4/    ጎልተው የወጡና በፌዴሬሽን ምክር ቤት፣ በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት፣ በፌዴራል መንግስት የሚመሩለትን የአስተዳደራዊ ወሰን ውዝግቦችን መርምሮ የውሳኔ ሃሳብ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ  እና ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ያቀርባል፤

5/    ከአስተዳደራዊ ወሰኖች ጋር በተያያዘ የተነሱ ግጭቶች ተፈተው፣ በአጎራባች ክልሎች መሃከል ያለው መልካም ግንኙነት የሚታደስበትና የሚጠናከርበትን መንገድ ያመቻቻል፤

6/    በቀጣይነት አስተዳደራዊ ወሰኖች የግጭት መንስዔ እንዳይሆኑ ሊወሰዱ የሚገባቸውን እርምጃዎች አስመልክቶ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ፣ለፌዴሬሽን ምክር ቤትእና ለሀዝብ ተወካዮች ምክር ቤት  ምክረ ሃሳብ ያቀርባል፤

7/    አስተዳደራዊ ወሰኖችና አካባቢያቸው አስተማማኝ ሰላም የሰፈነባቸው የልማትና የንግድ እንቅስቃሴ የሚካሂድባቸው እንዲሆኑ አስተዳደራዊ ወሰኖችን የተመለከተ የፖሊሲ ማእቀፍ ያመነጫል፤

8/    የአስተዳደር ወሰን ጉዳዮችን በተመለከት የህዝብ አስተያየት ይሰበስባል፤

9/    ጉዳዮ ከሚመልከታቸው የክልልና የፌደራል የስራ ሃላፊዎች፣ የፖለቲካ ቡድኖች፣ እንዲሁም ሌሎች ባላድርሻ አካላት አሰትያየትና ለጥናቱ የሚሆን ግብዐት ይሰብስባል፤

10/   ከህዝብ ግብዐትና አስተያየት የሚሰበሰብበትን አካሄድ የሚያሳይ፣ ሂደቱ ሁሉንም የህብረተሰብ ክፍል ያካተተ መሆኑን የሚያረጋገጥ ስትራትጂና ዝርዝር እቅድ ያዘጋጃል።

 1. የአስተዳደር ወሰንና የማንነት ጥያቄዎች

ማንኛውም የአስተዳደር ወሰን ውሳኔ፣ ራስን በራስ ማስተዳደርና የማንነት ጥያቄ በኮሚሽኑ ተጠንቶ አግባብነት ባላቸው ህጎች መሰረት ለፌዴሬሽን ምክር ቤት ቀርቦ እልባት ያገኛል፡፡

 1. ኮሚሽን አባላት አሰያየም

1/    የኮሚሽኑ አባላት ቁጥር በመንግስት የሚወሰን ይሆናል፡፡

2/    በኮሚሽኑ አባል ተደርገው የሚሰየሙ ግለሰቦች በስነ ምግባራቸው፣ በትምህርት ዝግጅታቸው፣ በስራ ልምዳቸው በማህበረሰቡ የተመሰገኑና መልካም ስም ያተረፉ ይሆናሉ፡፡

3/    የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፣ ምክትል ሰብሳቢ እና ሌሎች አባላት በጠቅላይ ሚኒስትሩ አቅራቢነት በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ይሰየማሉ።

 1. ኮሚሽኑ ስብሰባ

1/    የኮሚሽኑ መደበኛ ስብሰባ በየአስራ አምስት ቀኑ ይካሄዳል፣ ሆኖም እንደየ አስፈላጊነቱ በማናቸውም ጊዜ አስቸኳይ ስብሰባ ሊደረግ ይችላል፡፡

2/    ከኮሚሽኑ አባላት ከግማሽ በላይ የሚሆኑት ከተገኙ ምልዓተ-ጉባኤ ይሆናል፡፡

3/    የኮሚሽኑ ምክረሃ ሳቦች በስምምነት ያልፋሉ፡፡

4/    የዚህ አንቀጽ ድንጋጌዎች እንደተጠበቁ ሆኖ ኮሚሽኑ የራሱን የስብሰባሥነ-ሥርዓት ደንብ ሊያወጣይችላል፡፡

 1. የሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር

የኮሚሽኑ ሰብሳቢ፡-

1/    አጠቃላይ የኮሚሽኑን የስራ እንቅስቃሴ በበላይነት ይመራል፤

2/    ለኮሚሽኑ አስፈላጊ የሆኑ የድጋፍ ሰጭ ሠራተኞችንይመድባል፤

3/    ኮሚሽኑን በመወከል ከሌሎች አካላት ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡

 1. የምክትል ሰብሳቢ ስልጣንና ተግባር

የኮሚሽኑ ምክትል ሰብሳቢ፡-

1/    ሰብሳቢው በማይኖርበት ጊዜ ሰብሳቢዉን ተክቶ ይሰራል

2/    በሰብሳቢው የሚሰጡትንተግባራትይፈጽማል፡፡

 1. የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤት

1/የኮሚሽኑ ዋና ጽህፈት ቤት አዲስ አበባ ሆኖ እንደ አስፈላጊነቱ በሌሎች የሀገሪቱ ክፍሎች ቅርንጫፍ ሊኖረው ይችላል፡፡

2/    የኮሚሽኑ ጽ/ቤት በመንግስት የሚመደብ የጽ/ቤት ሃላፊ ይኖረዋል፡፡

 1. የጽህፈት ቤትስልጣንናተግባር

የኮሚሽኑ ጽህፈት ቤቱ የሚከተሉት ስልጣንና ተግባራት ይኖሩታል፡-

1/    ለኮሚሽኑ አጠቃላይ የአስተዳደርና ፋይናንስ አገልግሎት ይሰጣል፤

2/    ለኮሚሽኑ የምርምርና ጥናት አገልግሎት ይሰጣል፤

3/    ለኮሚሽኑ የህዝብ ተሳትፎና ምክክር መድረኮችን የሎጅስቲክስ ድጋፍ ይሰጣል፤

4/    የኮሚሽኑን ቃለ ጉባኤዎችን፣ ውሳኔዎችንና ሰነዶችን አጠናቅሮ ይይዛል፤

5/    የኮሚሽኑን ስራ ለማሳለጥ አስፈላጊውን ድጋፍና እገዛ ያደርጋል።

 1. የጽህፈት ቤት ሃላፊ

1/    የጽ/ቤቱን ሰራተኞች እናሃ ብትያስተዳድራል፡፡

2/    ለኮሚሽኑ አባላት የሚሰጡትን የሴክሪታሪያል እና ሎጅስቲክ ድጋፎች በበላይነት ይመራል፡፡

3/    የኮሚሽኑ እቅድና በጀት ያዘጋጀል በኮሚሽኑ ሲጸድቅም ተግባራዊ ያደርጋል፡፡

4/    ጽ/ቤቱን በመወከል ከሶስተኛ ወገኖች ጋር ግንኙነት ያደርጋል፡፡

 1. የኮሚሽኑ ገለልተኝነት

ኮሚሽኑ ስራውን በነፃነትና በገለልተኝነት ያከናውናል።

 1. የኮሚሽኑየሥራ ዘመን

1/    የኮሚሽኑ አባላት የስራ ዘመን እስከ እስከ 3 ዓመት ነው።

2/    በዚህ አንቀፅ ንዑስ አንቀፅ(1) የተጠቀሰው ቢኖርም የኮሚሽኑ የስራ ዘመንን እንደ ሁኔታው የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ሊያራዝመው ይችላል።

 1. የመተባበር ግዴታ

ማንኛውም ሰው ኮሚሽኑ በዚህ አዋጅ የተሰጠውን ሃላፊነት ለመወጣት በሚያደርገው እንቅስቃሴ ውስጥ ለሚያቀርበው ማንኛውም ህጋዊ እንቅስቃሴ ትብብር የማድረግ ግዴታ አለበት፡፡

 1. ጠቋሚዎችና ምስክሮችን ስለመጠበቅ

1/    ማንኛዉም ሰው በኮሚሽኑ ፊትቀርቦ በሚሰጠው ቃል መሰረት ክስ ሊመሰረትበት እንደዚሁም የሰጠው ቃል በእርሱ ላይ ማስረጃ ሆኖ ሊቀርብበት አይችልም፡፡

2/    ለጠቋሚዎችና ለምስክሮች ጥበቃ ለማድረግ የወጣ ሕግ ለኮሚሽኑ ቃላቸው እና መረጃ ለሚሰጡሰዎችም ተግባራዊ ይሆናል፡፡

 1. በጀት

የኮሚሽኑ በጀት በመንግስት ይመደባል፡፡

 1. ስለሂሳብ መዛግብት

1/    የኮሚሽኑ ጽ/ቤት የተሟላና ትክክለኛ የሆኑ የሂሳብ መዛግብት ይይዛል፡፡

2/    የኮሚሽኑ የሂሳብ መዛግብት እና ገንዘብ ነክ ሰነዶች በዋናው ኦዲተር ወይም ዋናው ኦዲተር በሚሰይማቸው ኦዲተሮች በየዓመቱ ይመረመራሉ፡፡

 1. ደንብና መመሪያ የማውጣትሥልጣን

1/    የሚኒስትሮች ምክር ቤት ይህንን አዋጅ ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ ደንቦችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

2/    ኮሚሽኑ ይህንን አዋጅና በዚህ አንቀጽ ንዑስ አንቀጽ (1) መሠረት የወጡ ደንቦችን ለማስፈጸም የሚያስፈልጉ መመሪያዎችን ሊያወጣ ይችላል፡፡

 1. አዋጁ የሚፀናበት ጊዜ

ይህ አዋጅ በፌዴራል ነጋሪት ጋዜጣ ታትሞ ከወጣበት ቀን ጀምሮ የጸናይሆናል።

አዲስ አበባ፤  ….. ቀን 2011 ዓ.ም.

ሳህለወርቅ ዘውዴ

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ ፕሬዝዳንት

 

ክሪሚናሊስቲክስ (criminalistics) ምንድነው?

ከ6 ወራት በፊት በመኪና /ባጃጅ/ አደጋ የተነሳ በእግሬ ላይ መጠነኛ ጉዳት ከደረሰ ወዲህ ብሎጌን update አላደረግኩም፡፡ አሁን አገግሜያለው፡፡ ለጠየቃችሁኝ ሁሉ ምስጋናዬ ይድረስ፡፡

ከ6 ወራት ቆይታ በኋላ በዚህ ብሎግ ከሚዳሰሱ ጉዳዮች ትንሽ ወጣ ባለ ርዕስ ላይ የውይይት በር ለመክፈት ሀሳብ አለኝ፡፡ ለውይይት የመረጥኩት ርዕስ ክሪሚናሊስቲክ ወይም ደግሞ ሁላችንም በምናውቀው ቃል ፎረንሲክ ሳይንስ ነው፡፡ የዛሬው ጽሑፍ አጠቃላይ ስለ ሳይንሱ እና ለፍትሕ ስርዓቱ በሚያበረክተው አስተዋጽኦ ዙሪያ ያጠነጥናል፡፡ መልካም ንባብ!

ክሪሚናሊስቲክስ (criminalistics) ምንድነው?

       ትርጓሜውና ይዘቱ

       የፎረንሲክ ሳይንስ መሰረታዊ ዕውቀት አስፈላጊነት

       ተሳስቶ ላለማሳሳት-የአስፈላጊነቱ ማሳያ

            የባሩድ ቅሪት በእጥበት ይለቃል?

            ወንጀል የተፈጸመበት የጦር መሳሪያ እንዴት ይታወቃል?

           የፖሊስ መግለጫ- ጉዳት አድራሹ ሽጉጥ ተለይቷል? 

ፋይዳው- ‘ከማዕከላዊ ወደ ላቦራቶሪ’

ፎረንሲክ ፓቶሎጂ /Forensic Pathology/

       ሞተናል የሚባለው መቼ ነው?      

ዋቢ መጻህፍትና ጽሑፎች

ክሪሚናሊስቲክስ (criminalistics) ምንድነው?

ትርጓሜውና ይዘቱ

እ.ኤ.አ. በ1248 ቻይና ውስጥ በሩዝ ማሳ ውስጥ ይሰሩ ከነበሩ ሰራተኞች መካከል አንደኛው በስሎት ተወግቶ ተገደለ፡፡ የገዳዩን ማንነት ለማወቅ ሁሉም የማሳው ሰራተኞች ለስራ የተሰጣቸውን ማጭድ እንዲያመጡ ተደርጎ በረድፍ ተደረደሩ፡፡ ከተደረደሩት መካከል አንደኛዋን ማጭድ ዝንቦች ወረሯት፡፡ በዚህን ጊዜ ገዳዩ ወዲያውኑ ተናዘዘ፡፡ ዝንቦቹ ያረፉት ደም የነካው ማጭድ ላይ ነበር፡፡ (Bertino, 2012) በዚሁ ዓመት እዛው ቻይና ውስጥ የህክምና ዕውቀትን ለህግ ጉዳዮች ተፈጻሚ የሚያደርግ የመጀመሪያው መጽሐፍ ተጻፈ፡፡ የመጽሐፉ ርዕስ በቻይንኛ Xi Yuan Ji Lu በእንግሊዝኛ ትርጉሙ The Washing Away of Wrongs and Collected Cases of Injustice Rectified  በሚል የሚታወቅ ሲሆን ጸሐፊው ሰንግ ትዙ (Sung Tz’u) ይባላል፡፡ ‘የማጭዱ ገዳይ’ ታሪክ በመጽሐፉ ውስጥ ከተዘገቡት ፎረንሲክ ጠቀስ ታሪኮች መካከል አንደኛው ነው፡፡ (Siegel & Mirakovits, 2010) ይህ መጽሐፍ በፎረንሲክ ሳይንስ ዕድገት ውስጥ የመጀመሪያው የተሟላ የፎረንሲክ ሳይንስ ማኑዋል /manual/ እንደሆነ ይነገርለታል፡፡ (Stefoff, 2011)

ክሪሚናሊስቲክስ የፎረንሲክ ሳይንስን ለወንጀል ጉዳዮች ተፈጻሚ የሚያደርግ ሳይንስ ነው፡፡ ቃሉ አንዳንዴ ከcriminology ጋር ይምታታል፡፡ ይሁን እንጂ criminology ወንጀል እና የወንጀል ባህርያትን የሚያጠና ማህበራዊ ሳይንስ እንደመሆኑ ሁለቱ ለየቅል ናቸው፡፡ (Fisher, Tilstone, & Woytowicz, 2009)

ለመሆኑ ፎረንሲክ ሳይንስ ምንድነው? ፎረንሲክ የሚለውን ቃል ብዙዎቻችን ሰምተነው እናውቃለን፡፡ ትክክለኛ ትርጓሜውን በተመለከተ ግን በብዙዎቻችን መረዳት ያለ አይመስልም፡፡ ለአንዳንዶች ፎረንሲክ ሳይንስ ሲባል የረቀቀና ጥቂት በሙያው የተካኑ ፖሊሶች ብቻ የሚረዱትና የሚጠቀሙበት ፖሊሳዊ ሳይንስ ነው፡፡ ይሁን እንጂ የፎረንሲክ ሳይንቲስት ለመሆን ፖሊስ ወይም መርማሪ መሆን አይጠይቅም፡፡ እንዲያውም ሳይንሱ በእግሩ እንዲቆም ያደረጉት የዘርፉ ፈር-ቀዳጆች አብዛኛዎቹ በፖሊስነት ሞያ ውስጥ አላለፉም፡፡

ፎረንሲክ ሳይንስ በአጭር አነጋገር ሳይንሳዊ ዘዴ በመጠቀም ከህግ አፈጻጸም የሚነጩ ጉዳዮችን ወይም ችግሮችን የሚፈታ ሳይንስ ማለት ነው፡፡ ሰፋ ባለ ትርጓሜው ለፍትሕ ስርዓት አገልግሎት የሚውል ማንኛውም ሳይንስ ሁሉ የፎረንሲክ ሳይንስ ነው፡፡ (Houck & Siegel, 2015) ከተፈጻሚነት አድማሱ አንጻር ሳይንሱ ለወንጀል ብቻ ሳይሆን ለፍትሐብሔር ጉዳዮችም ተግባር ላይ ይውላል፡፡ ሆኖም ሳይንሱ በጣም ጎልቶ የሚታየው ከወንጀል ምርመራ ጋር በተያያዘ ነው፡፡ ከዚህ አንጻር ካየነው በክሪሚናሊስቲክስ እና ፎረንሲክ ሳይንስ መካከል የረባ ልዩነት የለም፡፡ እንዲያውም ለአንዳንዶች ሁለቱም ተመሳሳይ ስያሜዎች ናቸው፡፡ (Stefoff, 2011)

‘fornesic’ የሚለው ቃል የመጣው forum ከሚል የላቲን ቃል ሲሆን ትርጉም ህዝባዊ ወይም የህዝብ ማለት ነው፡፡ በጥንታዊ ሮማ ሴኔቱ በፎረም /ህዝብ በሚሰበሰብበት ቦታ/ እየተገናኘ በፖለቲካና በፖሊሲ ጉዳዮች ላይ ክርክር /debate/ ያካሂድ ነበር፡፡ አሁን ድረስ በተለይ በአሜሪካ በህዝባዊ ክርክር /debate/ የሚወዳደሩ ተከራካሪ ቡድኖች /teams/ “forensics.” እየተባሉ ነው የሚጠሩት፡፡ (Houck,, 2007)

በነገራችን ላይ የመጀመሪያው የፎረንሲክ የሬሳ ምርመራ የተካሄደው እዛው ሮማ ውስጥ ነው፡፡ ጁሊየስ ቄሳር በጠላቶቹ 23 ጊዜ ተወግቶ ሲገደል አንቲሺየስ የተባለ ሐኪም የሬ ምርመራ ካደረገ በኋላ ቄሳርን ለሞት ያበቃችው የትኛዋ እንደሆነች ለመለየት ችሏል፡፡ (Evans, 2004) በፈረሲክ ሳይንስ ስር የሚታቀፉ ዘርፎች በጣም በርካታ ናቸው፡፡ ከእነዚህ መካከል ዋና የሚባሉት እንደሚከተለው ይዘረዘራሉ፡፡

 • ክሪሚናሊስቲክስ /Criminalistics/
 • ባለስቲክስ (Ballistics/ የጦር መሳሪያ ምርመራ /Firearm examination/
 • ፎረንሲክ የአጥንት ምርመራ /Forensic Anthropology/
 • ፎረንሲክ የጥርስ ምርመራ / Forensic Odontology/
 • ፎረንሲክ የሞት እና ሬሳ ምርመራ / Forensic Pathology/
 • ፎረንሲክ ሳይኮሎጂ /Forensic Psycology/
 • ፎረንሲክ የነብሳት /insect/ ምርመራ /Forensic Entomology/
 • ፎረንሲክ አካውንቲንግ /Forensic Sccounting/
 • ፎረንሲክ የአደጋ ምርመራ / Forensic Engineering/
 • የመርዛማ ነገሮችና አደንዛዥ ፅፅ ምርመራ /Toxicology/
 • ፎረንሲክ ባዮሎጂ /የደም፤ የፈሳሽና ዲ.ኤን.ኤ ምርመራ/ /Forensic Biology/
 • ፎረንሲክ ኬሚስትሪ /Forensic Chemistry/
 • የአሻራ ምርመራ / Ridgeology/
 • የሰነድ ምርመራ / Questioned Documents/
 • የወንጀል ስፍራ ምርመራ /Crime-Scene Investigation/