Category: law

የሰበር ችሎት የህግ ቃላት መፍቻ

የሰበር ችሎት የህግ ቃላት መፍቻ

የፌደራሉ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የሚሰጠው የህግ ትርጉም በየትኛውም ደረጃ ላይ በሚገኙ የክልል እና የፌደራል ፍ/ቤቶች የአስገዳጅነት ውጤት እንዲኖረው የፌደራል ፍርድ ቤቶች አዋጅን እንደገና ለማሻሻል በወጣው አዋጅ ቁ. 454/1997 ከተደነገገበት ጊዜ ጀምሮ ባሉት አስር ዓመታት ውስጥ ችሎቱ ካከናወናቸው አመርቂ ስራዎች መካከል ለህግ ቃላት ፍቺ ማበጀት አንዱና ዋነኛው ተደርጎ ሊጠቀስ ይችላል፡፡ ፈታኝ በሆነው ህግን የመተርጎም ስራ ውስጥ የቃላትንና ሐረጋትን ትክክለኛ ይዘት መወሰን እና የህግ ዕውቀት የሌለው ሰው በሚገባው ቀላልና አጭር አገላለጽ ትርጓሜያቸውን ማስቀመጥ ትልቁን ቦታ ይይዛል፡፡

አንዳንድ ቃላት ከህግ ጋር በተያያዘ ካልሆነ በቀር በዕለት ተዕለት የማህበረሰቡ የቋንቋ አጠቃቀም ግልጋሎት የላቸውም፡፡ ለምሳሌ ህግ ጠቀስ ባልሆነ ንግግር “እከሊት/ሌ እኮ ዳረገኝ/ችኝ” አንልም፡፡ መዳረግ፣ ዳረጎት ትርጉም የሚኖረው በህግ ግንኙነት ውስጥ ብቻ ነው፡፡ ለእነዚህና መሰል ቃላት በቀላሉ የሚገባ ፍቺ ካልተበጀ በስተቀር ህግ አዋቂውና የህግ ዕውቀት በሌለው የህብረተሰብ ክፍል መካከል መግባባት፣ መደማመጥ አይኖርም፡፡ አንዳንዴ በህግ ሙያተኛው ዘንድ ራሱ የህግ ቋንቋ የባቢሎን የሚሆንበት አጋጣሚ ይፈጠራል፡፡ አንዳንድ ቃላት በህግ አውጪው ሆነ ተርጓሚው ቁርጥ ያለ ትርጓሜ ስለማይሰጣቸው በአጠቃቀም ረገድ ልዩነት ይከሰታል፡፡ ለምሳሌ ከህግ ውጭ፣ ህገ-ወጥ፣ ህግ መጣስ፣ ህግ መተላለፍ፣ ህጋዊ ያልሆነ፣ የህግ መሰረት የሌለው የሚሉ ቃላትና ሐረጋት ጥቅም ላይ የሚውሉበት ሁኔታ ወጥነት አይታይበትም፡፡ Continue reading “የሰበር ችሎት የህግ ቃላት መፍቻ”

Who is ‘the government’?

Who is ‘the government’?

In Ethiopia, almost unlimited powers of rulemaking, rate fixing and appointing higher officials is reserved to ‘the government’. This body or person is neither the legislator nor the executive. It is unknown. It could not even be described precisely. However, its existence is for sure.

Any legislative act, for sake of clarity has to indicate ‘who does what?’ ‘The relevant authority will take relevant measures’ is no law at all. It is so obscure. And completely devoid of any meaning. In effect, senseless at all.

Vagueness and ambiguity is usually attributed to bad drafting error. However, the persistent and repetitive use of ‘the government’ and bestowing it significant powers doesn’t seem to be an error. When the law states that the Director General and Deputy Director Generals of the National Educational Assessment and Examinations Agency will be appointed by the government, it has to have in mind someone who will exercise this power. So, why not expressly state the Minister or higher official who will ultimately exercise the power of appointment? The answer is: Just like banks need legal reserve, the government also needs powers reserve. A deliberate negligence to disclose the power holder beforehand, facilitates the smooth and flexible allocation of powers according changing circumstances. Such flexibility allows the possibility of giving, taking, restricting or expanding powers at different times.

Here is a list of laws (though not exhaustive) in which the most important powers of administration are reserved to the ‘the government’ Continue reading “Who is ‘the government’?”

የኮምፒዩተር ወንጀል እና የጠቅላይ ዓቃቤ ህግ ማቋቋሚያ ረቂቅ አዋጆች

ረቂቅ አዋጆቹ በመስጠት ለተባበረኝ ብሎም የአሠሪና ሠራተኛ መጽሐፍ ረቂቁን አንብቦ ጠቃሚ ሂስ እና አስተያየት ለሰጠኝ ለጠበቃ ወረደ ኃይሉ (ድሬዳዋ) በዚህ አጋጣሚ ምስጋናዬን እገልጻለው፡፡

የኮምፒዩተር ወንጀልን ለመደንገግ የወጣ አዋጅ (ረቂቅ)

DOWNLOAD

የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዴሞክራሲያዊ ሪፑብሊክ ጠቅላይ ዓቃቤ ህግን ለማቋቋም የወጣ አዋጅ (ረቂቅ)

DOWNLOAD

አሠሪና ሠራተኛ ህግ፡ የሰበር ችሎት እንደተረጎመው

Update: መስከረም 4 ቀን 2012

መልካም ዜና! የታተመውን አሰሪና ሰራተኛ ህግ ጨምሮ ሶስት መጽሐፍትን ከ Google Play Store

ላይ በነጻ በማውረድ በሞባይላችሁ ላይ ጭናችሁ መጠቀም ትችላላችሁ። ለማውረድ ከዚህ በታች ያሉትን ሊንኮች ይጫኑ፡

 

 

 

አሰሪና ሰራተኛ ህግ

 

 

 

 

 

የአስተዳደር ህግ መግቢያ

 

 

 

በላልበልሃ፡ የጠበቃ ቀልዶችና የችሎት ገጠመኞች

 

 

 

 

The Revised Family Code of Ethiopia

 

 

 

 

Criminal Procedure code of Ethiopia

 

 

 

 

 

በ2008 ዓ.ም. ለፍሬ ለማብቃት ካቀድኳቸው ሥራዎች ውስጥ ሁለቱ ተጠናቀው አንደኛው ደግሞ ተገባዶ በማየቴ በተለምዶ ‘እጥፍ ድርብ’ የሚባለው ዓይነት ባይሆንም ትልቅ ደስታና እፎይታ ተሰምቶኛል፡፡ ይንንም ለ Ethiopian Legal Brief ጎብኚዎች በተለይም ደግሞ ለድረ ገጹ ቋሚ ተከታታዮች (followers and subscribers) ለማጋራት በማሰብ ብሎም ቅድመ ህትመት ለአንባቢ መተዋወቂያ ይሆን ዘንድ የአንደኛውን ሥራ የይዘት ማውጫ፤ የውሳኔዎች ማውጫ፤ የህግጋት ማውጫ፤ ዋቢ መጻህፍትና የቃላት ማውጫ ከቅንጭብ ጽሑፎች (የተመረጡ ገጾች) ጋር በዚህ ገጽ ላይ ለማቅረብ እወዳለው፡፡

በመጀመሪያ የሶስቱም ያልታተሙ ሥራዎች ርዕስና ገጽ ብዛት እነሆ!

  1. አሠሪና ሠራተኛ ህግ፡ የሰበር ችሎት እንደተረጎመው (ቅጽ 1 ገጽ ብዛት 411)
  2. የአስተዳደር ህግ መግቢያ (ገጽ ብዛት 265)
  3. Judicial and Statutory Definitions of Words and Phrases (365 pages)

አሠሪና ሠራተኛ ህግ፡ የሰበር ችሎት እንደተረጎመው

በዚህ ሥራ ከ1998 እስከ 2007 ዓ.ም. ድረስ የፌደራል ጠቅላይ ፍ/ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት የህግ ትርጉም የሰጠባቸው የታተሙ (ቅጽ 1 እስከ 18) እንዲሁም ያልታተሙ በጠቅላላይ ከ240 በላይ በሚሆኑ የሰበር ውሳኔዎች ላይ ዳሰሳ ተደርጓል፡፡ ልክ የዛሬ ዓመት የካቲት 2007 ዓ.ም. ላይ ሥራው ሲጀመር ከይዘት አንጻር ዋነኛ ትኩረት የተደረገው ገላጭ የሆነ ዘዬ በመከተል የሰበር ችሎት ትርጉም የሰጠባቸውን ጉዳዮች በየፈርጁና በየርዕሱ በመለየት የህጉን ይዘት በጥልቀት መፈተሸ ነበር፡፡ ሆኖም ‘የሌሎች አገራት ልምድ’ እንዲካተት ተደጋጋሚ አስተያየት በመቅረቡ ባደጉትና ባላደጉት አገራት የአሠሪና ሠራተኛ ህግ ይዘቱና አፈጻጸሙ በከፊል ተቃኝቷል፡፡

በመጽሐፉ ውስጥ የተጠቀሱ ህግጋትና የሰበር ውሳኔዎች በቀላሉ ማግኘት እንዲቻል የውሳኔዎች ማውጫ (Table of Cases) እና የህግጋት ማውጫ (Table of Legislations) ለብቻው ተዘጋጅቷል፡፡ የቃላት ማውጫው (Index) የቃላት ሳይሆን የተዛማጅ ርዕሰ ጉዳዮች መጠቆሚያ እንዲሆን ጥረት ተደርጓል፡፡

ማውጫዎቹንና የተመረጡ ጽሑፎችን ለማውረድና ለማንበብ DOWNLOAD የሚለውን link ተጫኑት፡፡

ማውጫ                             DOWNLOAD

የሰበር ውሳኔዎች ማውጫ              DOWNLOAD

የሕግጋት ማውጫ                    DOWNLOAD

ዋቢ መጻህፍትና ጽሑፎች             DOWNLOAD

የቃላት ማውጫ                      DOWNLOAD

የተመረጡ ገጾች                              

ዝውውር እና የአሠሪው ስልጣን፡ የሰበር አቋም ሲፈተሽ     DOWNLOAD

የኃይማኖት ተቋም ሠራተኞች                         DOWNLOAD

በጥፋት ምክንያት ሠራተኛን ስለማሰናበት         DOWNLOAD

የሥራ መደብ መሰረዝ                          DOWNLOAD